• Mon. Nov 9th, 2026

በምስራቅ እና በምዕራብ አርሲ ዞኖች ውስጥ የፋሺስት ብልፅግና ቡድን ሰላማዊ ኦሮሞዎችን አስሮ ማሰቃየቱን ቀጥሏል

Sep 1, 2024

ነሐሴ 31፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በምስራቅ እና በምዕራብ አርሲ ዞኖች ውስጥ ኦሮሞዎችን ያለምንም ገደብ አስሮ እያሰቃያቸው ይገኛል። ይህንንም የግፍ ተግባር የሚተገብረው “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትደግፋላችሁ”፣ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን አቋም እና አመለካከት አለህ/አለሽ”፣ “ባለቤትሽ የኦነሰ አባል ነው።” በሚል የተለያየ የውንጀላ መርሆን በመቅረፅ ነው። ወደ እስር ቤቱ ካጎራቸው እና ከሚሰቃዩት መሃከል ስማቸውን አቢኦ ያገኘው የሚከተሉት ናቸው።

ምስራቅ አርሲ ዞን

ጃጁ ወረዳ 

ነሐሴ 1፣ 2024 ከፊንጮ ቀበሌ ሁለት ቄሮዎችን: ጫጮሌ በያን እና Dhaቀቦ ረሻድ የተባሉትን ከ ኦነሰ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሃሰት ውንጀላ ከስራ ቦታቸው እየደበደቡ በመውሰድ በፖሊስ ጣቢያቸው አስረው እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ። 

ጎሎልቻ ወረዳ

በጎልቻ ከተማ ከ100 በላይ ንፁሃን ኦሮሞዎች በኦሮሞነታቸው አለመደራደራቸው ብቻ የ የኦነሰ አመለካከት አለህ/አለሽ ብቻ በማለት እስር ቤት ውስጥ ከሶስት ወር በላይ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ከእነዚህም ውስጥ አቢኦ ስማቸውን ያገኘው፦

  1. ምስባ ሽመልስ፣
  2. ማፊስ አብዲ እና
  3. ሴፋ አልዪ ብቻ ነው።  

ሐምሌ 24፣ 2024 የሁለት ህፃን ልጆች እናት የሆነችውን አዴ ኑርያ ሀሰንን “ባለቤትሽ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል ነው።” በማለት በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ አስረው እያሰቃዩዋት ይገኛሉ።

ምዕራብ አርሲ ዞን

አዳባ ወረዳ ሐምሌ 31፣ 2024

  1. ሼምሱ አብዱላሂ፣
  2. መሐመዱሴን አብዱላሂ፣
  3. ኢንዲሪስ ሳዴ፣
  4. ጆቢር ሳዴ እና
  5. ኡመር ሃጂ ዩኔ ታስረው እየተሰቃዩ ሲሆን፤

ይህንን ግፍ ማለትም የፋሺስት ብልፅግና ጦርን ጋብዘው የሚያስፈፅሙት አወል ጀሙ እና አማዳ ሀሙ የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልፀዋል። 

ሻሸመኔ ከተማ ቀበሌ 81 ሐምሌ 31፣ 2024

  1. ኡርጌሳ ከዲር፣
  2. ከማል ሹንካ፣
  3. ኡሴን ዋንባሪ፣
  4. አማን ገለቱ፣ እና
  5. አብዱላሂ ቲቤሶ ታስረው እየተሰቃዩ ሲሆን፤ 

እነዚህ ንፁሃን በቀን አንድ ግዜ፣ በተወሰነ ሰዓት ብቻ ወደ ሽንት ቤት እንደሚወሰዱና ከዚያም በሁዋላ እስር ቤቱ ውስጥ እንደሚቆለፍባቸው እና ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉም እንደተወሰነባቸው አቢኦ ከምንጮቹ ተነግሮታል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

#ጨቋኙ_ኃይል_በኦነሰ_ኃይል_ይገረሰሳል!

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

Leave a Reply