• Sat. Mar 14th, 2026

በምሥራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን ጦር የኦሮሞን ህዝብ ማሰር እና ማሰቃየት ቀጥሏል

Aug 31, 2024

ነሐሴ 28፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)  

የብልፅግናው ቡድን ጦር የኦሮሞን ህዝብ ማሰር፣ ማስቃየት እና መግደልን አጠናክሮ ቀጥሎዋል። ለዚህም ምክንያት የሚሰጠው ከኦነሰ ጋር፥ ግንኙነት አላችሁ፣ ትረዳላችም በሚል የሃሰት ውንጀላ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል። 

ምሥራቅ ወለጋ ዞን

ሐምሌ 27፣ 2024 በሃሮ ሊሙ ወረዳ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባንዲራ ያለበት ስኒ እቤት ውስጥ በማየታቸው “እናንተ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ደጋፊዎች ናችሁ።” በማለት ታጆ አደም እና ሙሳ ኑጉሴ የሚባሉ ሰዎችን እስር ቤት አስገብተው እያሰቃዩዋቸው ይገኛሉ። የሁለቱ ንፁሃን በቁጥጥር ስር ማድረግ፣ የወረዳው የመገናኛ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዜናውን እንደ ድል ዜና ማለትም ልክ የኦነሰ አባልን እንደያዙ በማስመሰል አቀነባብሮ በሚዲያቸው እንዲዘገብ እድርጎዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባንዲራ በኢምፓየሪትዋ ህግ መሰረት በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ያለ ቢሆንም የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን ዛሬም በዚህ ባንዲራ ስም ማህበረሰቡን እያሰቃየ ይገኛል።

ከላይ ከተጠቀሰው ውጪ ሐምሌ 27፣ 2024 በምሥራቅ ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ላይ ሰላማዊ ሰዎችን ወደ እስር ቤት ከተወሰዱት በከፊል ስማቸውን አቢኦ ከእካባቢው ነዋሪዎች ያገኘው፦

  1. ራኡፍ ጂሀድ፣
  2. አልዪ ጀማሎ፣
  3. ኢብሳ ጀማል፣
  4. ኢስክንዲር አብደላ፣
  5. ሸሪፍ አብደላ እና
  6. መሀመድኑር በያን ናቸው።

ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን 

በተመሳሳይ ሁኔታ በጉዱሩ ወረዳ ውስጥ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እናጠፋለን!” በሚል የዘመቻ ስም የተሰማሩት የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድኖች ሰላማዊውን የኦሮ ማህበረሰብ ማሰር እና መግደል ቀጥለውበታል።

ሀምሌ 26፣ 2024 ከታሰሩት ውስጥ ስማቸውን አቢኦ ያገኘው፦

  1. ቢራኔ ሻንቆ
  2. ሚሬሳ ሻንቆ
  3. ጀቤሳ ጉደታ እና
  4. ረታ የሚባሉ ሲሆን በፖሊስ ጣቢያው በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም ታስረው እየተሰቃዪ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

#ጨቋኙ_ኃይል_በኦነሰ_ኃይል_ይገረሰሳል!

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading