• Wed. Apr 22nd, 2026

ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምስራቅ እና በምዕራብ አርሲ ዞኖች በወሰደው የማጥቃት እርምጃ 19 የጠላት ጦርን ከአፈር ቀላቅሎ 30ውን በማይሽር ቁስል ሸኝቷል

Sep 30, 2024

መስከረም 28፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻ የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት፣ የጃል ነdhii ገመዳ ጭብራ ሰላማዊ ህዝብን ሲያሰቃይ የነበረውን የጠላት ኃይል በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ ዞኖች ውስጥ እያራገፈ ይገኛል።

ምስራቅ አርሲ ዞን

መስከረም 19፣ 2024 በሙኔሳ ወረዳ፣ ዳሙ ቀበሌ ውስጥ ጠዋት በማለዳ ወደ ሙኔሳ ወረዳ ከተማ ቀርሳ በሚያደርሰው ትልቁ መንገድ ላይ የኦነሰ አድፍጦ በመጠበቅ የፈራረሰችውን የኢትዮጵያን ኢምፖየር ለማስቀጠል ዘብ ሆኖ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የብልፅግና ጦር 13ቱን ሲገድል 19 አቁስሎ ሸኝቷል። 

ከዚህም በላይ ተሽከርካሪዎቻቸውንም ከአገልግሎት ውጪ ማድረጉን የጦሩ ቃል አቀባይ ለአቢኦ አሳውቋል።

ምዕራብ አርሲ ዞን 

መስከረም 19፣ 2024 ከሄበን ወረዳ ወደ ምስራቅ አርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ስትጓዝ የነበረውን የፋሺስት ብልፅግና ጦር አድፍጦ በመጠበቅ አንድ 3F መኪና እና አንድ FSR አውድሟል።

መስከረም 12፣ 2024 በገደብ አሳሳ ወረዳ፣ ሁሉቆ ቀበሌ ውስጥ ህዝብን አንድ ላይ በመሰብሰብ ሲያሰቃይ የነበረውን የፋሺስት ብልፅግና ጦር ላይ በወሰደው የደፈጣ ማጥቃት እርምጃ 6 የኢምፓየሯን ወታደሮች በመግደል 11 በማይሸር ቁስል ሸኝቷል። የተረፉትም ወደ ወረዳው ከተማ ፈርጥጠው ሄደዋል።  

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading