ጥቅምት 1፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
መስከረም 18፣ 2024 አንበሳው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ በሱሮ በርጉዳ ወረዳ፣ መከላ ቀበሌ ውስጥ በፋሽስት አብይ አህመድ ጦር ላይ በተጠቀመው ታክቲካዊ የጦር ስልት የማያዳግም እርምጃን በመውሰድ ብዙዎቹን በሙት እና በቁስለኛ ቀጥቷል።
በዚህ ጦርነት የተመታው የጠላት ሃይል የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለማሰስ በሚል የተሰማራ ሲሆን አንበሶቹ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊቶች ለወንጀል የተሰማሩበትን አካባቢ በመክበብ ሳይወዱ በግዳቸው ወደ ካምፓቸው እንዲሸሹ በማድረግና እነሱንም በመከተል አብረው ካምፓቸው ገብተዋል። እዚያም ውስጥ የገደሉትን ገድለው፣ የተወሰኑትን አቁስለው የተረፉት ሙታቸውንም ሆኑ ቁስለኞቻቸውን ሳያነሱ ከካምፑ ወጥተው ጀግናው ስራዊታችን ካምፑን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮት ይገኛል።
መስከረም 17፣ 2024 በገላና አበያ ወረዳ፣ ጋንጎዋ በሚባል ስፍራ በርካታ ቁጥር ያላቸው የፋሺስት ብልፅግና ጦር ደህንነቶቻቸውምን ጨምሮ ጋር በሙት እና በቁስለኛ ቀጥቷል።
ከዚህም በላይ ለቀበሌ መዋቅር ግንባታ የተሰማሩት ካድሬዎች/ካቢኔዎች በመደናገጥ ከአካባቢው ተነቅለዋል።
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል!
ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!
