• Sat. May 2nd, 2026

በምዕራብ ወለጋ ዞን የፋሺስት ብልፅግና ጦር ንፁሃን ኦሮሞዎችን መግደሉን ሲቅጥል፣ ከካድሬዎቹ ጋር በማበርም ህዝብ ለመዝረፍ ሲመካከሩ ቢሰንብቱም ከ10 በላይ የብልፅግና ካቢኔዎች ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል 

Oct 13, 2024

ጥቅምት 2፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ዩብዶ ወረዳ 

መስከረም 22፣ 2024 አለጉ ደጎማ ቀበሌ ውስጥ የፋሺስት ብልፅግና ጦር ገዳይ ቡድን ሁለት ቄሮዎችን ጥይት እንደ ዝናብ በማርከፍከፍ በሚያሰቅቅ መንገድ በህዝብ ፊት ገድለዋቸዋል። የተገደሉትም ቄሮ ዮና ዋሪን እና ሁለተኛውን ለጊዜው ስሙን አላገኘንም። 

መነ-ሲቡ ወረዳ 

በምዕራብ ወለጋ ዞን በመነ-ሲቡ ወረዳ በመንዲ ከተማ ውስጥ ነሃሴ 7፣ 2024 ካቢኔዎቹ እና የጦር መሪዎች አንድ ላይ በመሆን እንዴት በአከባቢው የገጠር ህዝብ ላይ ዝርፊያ እንደሚያካሄዱ ሲመካከሩ የቆዩ ሲሆን የወረዳው አስተዳዳሪ ገመችሴ ሲርቃ ጨምሮ የሚሰሩባቸውን ቀበሌዎች ሲከፋፉሉ መቆየታቸውን ምንጮቻችን ለአራታ ቢዮሌሳ ገልፀዋል።

በመነ-ሲቡ ወረዳ ባሉት ቀበሌዎች ውስጥ በመዘዋወር በግብር ስም ገንዘብ እንደሚሰበስቡም ሲመካከሩ ውለዋል። ውሳኔያቸውም በአንድ ቀበሌ ሰባ፣ ሰባ ወታደሮች በመመደብ ውሳኔያቸውንም ለመተግበር  ዝግጅት ላይ እንዳሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ።

ባቦ ገምቤል ወረዳ

በባቦ ገምቤል ወረዳ ውስጥ ለልማት ፕሮጀክቶች በጀት ተመድቦ የነበር ቢሆንም በወረዳው ምንም ዓይነት የልማት እንቅስቃሴ አልታየም። ይህንንም በተመለከተ በኦሮሚያ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና በባቦ ገምቤል የብልፅግና ካቢኔዎች መካከል በተፈጠረው አለመግባባትም የፀረ-ሙስና ኮሚሽኑ “መድበን የነበረውን በጀት መልሱ። ምክንያቱም ምንም የተከናወነ ፕሮጀክት ምድር ላይ አናይም፣ ይህም ማለት የመንግስትን በጀት ለራሳችሁ ጥቅም አውላችኋል።” በማለት ነሃሴ 5፣ 2024 በባቦ ገምቤል ወረዳ ከ10 በላይ የብልፅግና ከፍተኛ አመራርን ወደ እስር ቤት መወርወራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል።

ዝርፊያውን ፈፅመዋል በማለት ወደ እስር ቤት የተወረወሩትም፦

  1. ሃፍታሙ ሞሲሳ የልማት እና ምጣኔ ሀብት ቅንጂት ኃላፊ
  2. ሚናሴ ሙሉሰው የስራ ዕድል ፈጠራ እና ሙያ ኃላፊ
  3. መልካሙ ራጋ የውሃ ክፍል ኃላፊ
  4. አበቤ ሰንበታ አስተዳደር
  5. ድንቄ ታዬ የባህል እና ቱሪዝም ኃላፊ
  6. ሀብታሙ ገመቺስ የግብርና ኃላፊ
  7. ተሰማ ዲንቃ የትምህርት ክፍል ኃላፊ
  8. ገዛኸኝ ፍቃዱ የብልፅግና ፅ/ቤት
  9. ቢጂጋ አበራ እና 
  10. ሀሰን ኢንዳሉ የጤና ጥበቃ ኃላፊዎች መሆናቸው ታውቋል።

የብልፅግና ካቢኔዎች ገንዘብ ከህዝብ ላይ ለመዝረፍ አንድነት ሲኖራቸው በሚከፋፈሉበት ግዜ ልዩነታቸውን ያሰፋሉ እንጂ ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉትን ችግሮች ሰላምን ጨምሮ አንዱንም ለመፍታት ፍላጎትም ሆነ አቅም የሌላቸው መሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading