• Tue. Apr 28th, 2026

⚠የኦሮምያው የአብይ ድራማ⚠ – ከካሃዲዎቹ ጋር የኦሮሞ ነዓነት ሰራዊት ያባረራቸውን 62 ተባባሪዎችን (የድርጅታችን የቀድሞ አባላትን) “ስትራቴጅካሊ” ለመጠቀም ሞክረዋል

Dec 6, 2024

የአብይ አህመድ የካድሬ ስብስብ የሚያሰረጨውን የፕሮፓጋንዳ ፎቶዎች እና ቭድዮዎችን በጥሞና ተመለከትን። ትንሽ መሻሻል አለ። (We give credit where credit is due!) ከካሃዲዎቹ ጋር የኦሮሞ ነዓነት ሰራዊት ያባረራቸውን 62 ተባባሪዎችን (የድርጅታችን የቀድሞ አባላትን) “ስትራቴጅካሊ” ለመጠቀም ሞክረዋል።

ባሰራጯቸው ፎቶዎች ሁሉ እነዚህን 62 ግለሰቦችን ከፋፍለው በመጀመሪያው ረድፍ አሰልፈዋል። ውስጥ አዋቂዎችን ጭምር ለማደናግር የታሰበች ከነአብይ እና ሸመልስ ትንጥዬ ጭንቅላት የወጣች “ጅኒየስ” ቅንብር መሆኗ ነው። ከ62ቱ ጀርባ የተሰለፉት፣ 1) የሽመልስ የ“ሸኔ” የሽፍታ ስብስብ 2) ከማረምያ ቤቶች የተሰባሰቡ ታራሚዎች እና 3) በፍቃድም ሆነ ተገዶ የተሰለፉ ዊግ-ለባሽ የከተማና የገጠር ላባደሮች ናቸው።

ቀጥሎ ያደረጉት እነኝን ለፎቶ የተሰናዱ ቅንብሮች በኣውቶቢስ ከኣንድ ወረዳ ወደ ሌላ ወረዳ (ጥቂት ፊት ለፊት የሚታዩ ሰዎችን እየቀያየሩ) ቪድዮ ያስቀረጻሉ። ይሄንኑ ድራማ በየቀኑ በተመሳሳይ ይደግማሉ። ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በውሃላ ካቀናበሩት የ”ዋሚ/ያሚ” ስክረፕት እና ከደራው የሰው ልጅ እርድ በውሃላ ኣቅደው ከነበረው ተውኔት ጋር ኣንድ እና ያው ነው። #Oromia #Ethiopia

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading