• Fri. May 15th, 2026

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በመላዉ ኦሮሚያ የፋሽስቱን ስረዓት የማፅዳት ሰፊ ዘመቻ እያካሄደ ነዉ

Nov 6, 2022

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በመላዉ ኦሮሚያ የፋሽስቱን ስረዓት የማፅዳት ሰፊ ዘመቻ እያካሄደ ነዉ::

ONM- ABO – November 06/2022

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በመላዉ ኦሮሚያ ሰሞኑን በተመሳሳይ ዘመቻ በከፈቱት “የፋሽስቱን ሀይል የማፅዳት ዘመቻ” አጠናክረዉ መቀጠላቸዉ ተገለፀ:: የፋሽስቱን ሀይል ከኦሮሚያ ክልል የማፅዳት ዘመቻዉ ዛሬም እየተደረገ ሲሆን በዛሬዉ እለት በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን በምዕራብ ኦሮሚያ የምስራቅ ወለጋን ዞን ዋና ከተማ ነቀምቴን የተለያዩ ክፍሎች የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የፋሽስቱን ሰራዊት በማፅዳት ተቆጣጥሯል:: በዚህ ኦፕሬሽንም ከጃቶ ማረሚያ ቤት, ከተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች እና ከኩምሳ ሞረዳ ጥንታዊ ቤተ መንግስት ምድር ቤት በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ነፃ ማዉጣቱም ተገልጿል::

በከተማዋ እና ዙሪያዋ በተደረገዉ ከባድ ፍልሚያ ደግሞ በከተማይቱ የተለያዩ አከባቢዎች ካምፕ ሰርቶ የኦሮሞን ህዝብ ሲያሰቃይ የነበረዉ የፋሽስቱ ቡድን ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ የተበተኑ ሲሆን በንፁሃን ላይ ደስታቸዉን ለመግለፅ ወጥተዉ በተባራሪ ጥይት ከተመቱት ዉጪ የደረሰ ጉዳት እንዳሌለም ተገልጿል::

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (WBO) በተመሳሳይ ኦፕሬሽን በምስራቅ ኦሮሚያ ሀረርጌ ዞኖች ዉስጥም ተመሳሳይ ድሎችን ያገኘ ሲሆን በኩርፋ ጨሊያ ወረዳም የፋሽስቱን ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል::

በመዓከላዊ ኦሮሚያ (ሸዋ ዞኖች) የተለያዩ ቦታዎች ላይ የፋሽስቱ ቡድን እየተደመሰሰ ሲሆን በምዕራብ ሸዋ(ጂባት ፣ ሲልካምባ ፣ ኖኖ) በፋሽስቱ በብልፅግና ሰራዊት እና በWBO መካከል ከፍተኛ ትግል እየተደረገ ነዉ::

በምዕራብ ወለጋ የዛሬዉን ሳይጨምር በዚህ 15 ቀን ብቻ 10 ወረዳዎች ከፋሽስቱ ሰራዊት ፀድቶ ህዝባዊዉ ሀይል የተቆጣጠራቸዉ ሲሆን የህዝብ እንደራሴዎችም ከህዝቡ መሃል ተመርጠዉ ለግዜያዊ አስተዳዳሪነት እየተሾሙ ነዉ:: ከኦፕሬሽኑ በተጨማሪም የገበያ እቀባ አድማ በWBO እና ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ የተጠራ ሲሆን እጅግ በርካታ ቦታዎች የንግድ እንቅስቃሴም ሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል:: አምስት ቀን የሚፈጀዉ የገበያ አድማም በተሳካ ሁኔታ በተናበበ መልኩ እየተደረገ ነዉ ተብሏል::

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading