• Fri. Apr 19th, 2024

የታንዛንያውን የሰላም ድርድር አስመልክቶ ከኦነግ-ኦነሰ የተሰጠ መግለጫ

May 3, 2023

በኦሮሚያ ያለውን ግጭት ለመፍታት ያለመ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር – በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል፣ በታንዛንያ የተጀመረው የመጀመርያው ዙር የሠላም ድርድር ዛሬ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቋል። አንዳንድ በተነሱ
ጉዳዮችላይመግባባትላይየተደረሰቢሆንም፣ በዚህዙር የውይይት መድረክ አንዳንድ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም።

ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን በዘላቂነት እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በማሰብ ውይይቱን ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም አምነዋል። ኦነግ-ኦነሰ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ግጭቱን በዘለቄታዊነት እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ትርጉም ያለው ፖለቲካዊ እልባት እንዲያገኝ፣ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል።

ኦነግ-ኦነስ ውይይቱን ላመቻቹ እና ላስተናገዱትም አካላት ሁላ ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።


የኦነግ-ኦነሰ ከፍተኛ አዛዥ

ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading