• Wed. Mar 11th, 2026

በአብይ አህመድ መራሹ ብልፅግና ቡድን ድጋፍ፣ ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራው የአማራ ጽንፈኛ ቡድን በሰሜን ኦሮሚያ ወሎ ላይ እያካሄደ ያለው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

Mar 21, 2024

መጋቢት 21/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የወሎ ኦሮሞ ለማንነቱ ሲል ለብዙ ዘመናት የሕይወት መስዋዕትነትን እየከፈለ፤ እንዲሁም ሀብት ንብረቱ እጋየበት፣ የሰቆቃ ሕይወት እየኖረ ለዛሬ ደርሷል። ይህ አልበቃ ብሎ ዛሬም እነዚሁ የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎች በኦሮሞ ጠሉ አብይ አህመድ እየተደገፉ የወሎ ኦሮሞን መስዋዕት እያደረጉ፣ ቤት ንብረቱን እያቃጠሉበት፣ እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ የለፋበትን ሰብል ማሳው ላይ እያጋዩበት ይገኛሉ። እንዲህ ዓይነት የተቀናጀ የማወደም ዘመቻ በህዝባችን ላይ ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም የአሁኑ ግን በሕይወት እና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

የአከባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ይህ ግጭት እስከዚህች ሰዓት ድረስ እንዳልቆመና የብልፅግናው አመራር ህዝቡን ከጥቃት ለመከላከል ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳልወሰደ፣ እንዲሁም ምንም ዓይነት ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ድጋፍ እንዳላደረገለት፣ ሲገልጹ ይህም የሚያመለክተው እነዚህን ታጣቂዎች እየደገፈና እያስታጠቀ ለዚህ የጥፋት ተልዕኮ ያሰማራቸው ራሱ የብልፅግና አመራር ሳይሆን እንዳልቀረም ገልፀዋል።

ለዚህም ማስረጃ መጥቀስ ካስፈለገ፣ ባለፉት ቀናት የኢምፓየሪቱ መከላከያ ኃይል የተባሉቱ ሰላማዊዉን ሕዝብ ከፋኖ ተብዬው የጥፋት ቡድን ጥቃት መከላከል ሲገባቸው ህዝባችን ከፊት ፋኖን ሲከላከል እነርሱ ከኋላ ተኩስ በመክፈት አራት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለው ከ10 በላይ ሰዎችን አቁስለዋል።

በተጨማሪም እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በራማድን ጾም ወቅት ሕዝቡን ሰላም ለመንሳት እስከ ቀዬዉ መጥተዉ ጦርነት በመክፈት ንፁሃንን ሲጨፈጭፉ የብልጽግናው አመራር ዝም ብሎ ከማየትም በላይ ከጠላት ጋር አብሮ በጀርባ በኩል ግድያ መፈፀሙ ወረራው እየተፈፁመ ያለው በጥምር ኃይል መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

መጋቢት 19/2024 በጂሌ Dhuሙጋ በሰላማዊው ህዝባችን ላይ ተከፈቶ የነበረው ከባድ ውጊያ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶአል፤ ስለሆነም  መላው የኦሮሞ ህዝብ በሚችለው ሁሉ ከጎናችን እንዲቆም በማለት መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading