ደጋግመን እንዳስጠነቀቅነው በሆሮ ጉዱሩ እና በምስራቅ ወለጋ በሰላም አብሮ ሲኖር የነበረ ህዝብ ሆን ተብሎ የጭፍጨፋ አዙሪት ውስጥ እንዲኖር ተደርጓል። እየፈሰሰ የቀጠለው የንጹሃን ደም አብይ አሕመድ ከመምጣቱ በፊት ሊደረግ ይቅርና ሊታሰብም የሚችል አልነበረም።
የሰሞኑ እልቂት የጀመረው መጋቢት 4, 2026 በአብይ የተኮለኮለው እና የሚደግፈው ‹ፋኖ በወለጋ› ተብዬ ቡድን፡ በአቤ ዶንጎሮ ውረዳ አራት ቀበሌዎች ንጹሃን ኦሮሞዎችን ስጨፈጭፍ ነው። ገዳይ ቡድኑ 180 ቤቶችን አቃጥሎ፣ ሶስት ሰላማዊ ዜጎችን ገድሎ (ከእነዚህም መካከል የሶስት ወር አራስ) እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤት እንስሳትን ዘረፈ።
ከ 2 ቀናት በኋላ የመከላከያ መኮንኖች፣ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል እና በጃል ሞሲሳ ተብዬ የሚመራ ሸኔ ገዳይ ቡድንን “መበቀል አለብን” ብሎ በማሰባሰብ የአማራ ማህበረሰብ በሚበዛበት አሩሴ ቀበሌ ዘልቀው በመግባት 200 ቤቶችን አቃጠሉ።
በአማራ ክልል ፋኖ ላይ ሰፊ ጦርነት የከፈተው የአብይ አገዛዝ፣ ወለጋ ውስጥ ግን እራሱ አደራጅቶ፣ እንዲኖር የፈቀደለትን “ፋኖ” ተጠቅሞ ኦሮሞን ያስጨፈጭፍና ወዲህ ዞር ብሎ፣ “አማራ ጨፈጨፈህ” እያለ የኦሮሞን ሕዝብ አጠገቡ ባለ አማራ ላይ፣ አለፍ ብሎም “መከላከያ ተቀላቅለህ ሩቅ ያለውን አማራ ተበቀል” እያለ ይቀሰቅሳል።
ሁለቱም “ፋኖ በወለጋ” እና አሁን በሞሲሳ የሚመሩት ሸኔ ገዳዮች የአብይ ኦህዴድ ተቀጥላ ናቸው። እያንዳንዱ የተቃጠለ መኖሪያ፣ የእያንዳንዱ የእምቦቅቅላ ሬሳ፣ የወደመው አንጡራ ሀብት አላማው አንድ ነው፡- ኦሮሞን እና አማራን፣ እንደ ህዝብ እና የፖለቲካ ማህበረሰብ ሊያመልጡት የማይችሉት የበቀል አዙሪት ውስጥ ማስገባትና በመሃል ዘውድ ለማጽናት የተተበተበ የጭካኔ ሴራ ነው።
መፍትሄው ቀጥተኛ ነው፡ ሁሉም የሀገሪቱ ህዝቦች ይህንን ደም መጣጭ አገዛዝ በመተባበር ማስወገድ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ሃይሎች እነዚህን ደባዎች በአደባባይ በማያሻማ መልኩ እንድታወግዙ እና ከአገዛዙ የፍጅት ተወካዮች እራሳችሁን እንድታርቁ ጥሪ እናቀርባለን።
የኦነግ-ኦነሰ ከፍተኛ ዕዝ
መጋቢት 10, 2026
#Oromia #Ethiopia
