• Wed. Mar 11th, 2026

“ፋኖ” ብሎ ራሱን የሚጠራው ፅንፈኛ እና ተስፋፊ የአማራ ቡድን በመስራቻቸው በአቢይ አህመድ መራሹ መንግስት ታጣቂዎች እየተደገፈ በወሎ ኦሮሞ ላይ የከፈትውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥለዋል

Mar 24, 2024

መጋቢት 24/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በፋሽስት አብይ አህመድ የተነደፈዉ መርሆ፦ “የወሎ እሮሞዎችን ማንነት ማጥፋት እና መሬታቸውን መቀራመት” ሲሆን ይህንን መርሆ እውን ለማድረግ “ፋኖ” ብሎ ራሱን የሚጠራው ፅንፈኛ እና ተስፋፊ የአማራ ቡድን ከአብይ አህመድ መራሹ ቡድን ታጣቂዎች ጋር ተቀናጅተው እየተገበሩት ይገኛሉ። በተለይም በዚህ በወረሀ ረመዳን ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም በንፁሃን ሕዝብ ላይ እያካሄዱ ባሉት ጦርነት የኦሮሞ አርሶኣደሮችን ለህልፈት እና ለከባድ ቁስል ዳርገዋል። ከዚህም በላይ ቤታቸውንና ማጓጓዝ ያልቻሉትን ንብረታቸውን በእሳት ማውደምን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው አድርገዉታል ።

በዚሁ ሁኔታ መጋቢት 20/2024፣ እነዚሁ የተቀናጁ አካላት ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ማታ 12:00 ድረስ ልዩ ስሙ ሰዴን መካና (ሀጣዬ ከተማ) በሚባል ቦታ ብቻ በከፈቱት ጦርነት ዘጠኝ ሰዎችን ገድለው ሀያ አንድ ሰዎችን አቁስለው ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀ ድረስ በእነዚህ በታጠቁ ፅንፈኛ የአማራ የጥፋት ኃይሎች የተገደሉት የኦሮሞ ልጆች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ስናቀርብ ለቤተሰቦቻቸው ለዘመድ አዝማዳቸው ጽናትን እየተመኘን ነው፦

  1. ካሊድ አደም ኡስማን የሰባት (7) ዓመት ህፃን ጃራ ዋታ ቀበሌ፣
  2. አልዪ አደም አልዪ ሰንበቴ ከተማ፣
  3. ሁሴን አልዪ ሙሴ ሉጎ ቀበሌ፣
  4. አማደኔ ሙሳ ሀሰን ሀጣዬ፣
  5. ሁሴን ሞሐመድ አሊዮ፣
  6. አሂመድ ሙሳ ሀሰን፣
  7. ኢብራሂም አሊ ሙሳ፣
  8. ሀሰን አደም ስራጁ ጃራ ዋታ ቀበሌ፣
  9. ሁሴን ሞሐመድ አሊዬ ዝግባ ቀበሌ፣
  10. ሀሰን አደም ቢላል ሉጎ ቀበሌ፣
  11. አልዪ አደም አልዪ ወረ ባቦ ቀበሌ፣ እና
  12. አወሌ የተባሉት የተገደሉ ሲሆን 

ከቆሰሉት ሰዎች መካከል ደግሞ፦ ሀሰን አብደሌ፣ አሜ ሻፊ እና ሞሐመድ አልዪ ዲማ ከዝግባ ቀበሌ ናቸው።

በፋሽስት አብይ አህመድ አሊ የሚደገፈው ፅንፈኛው የአማራ ፋኖ ታጣቂ ቡድን ከባድ የጦር መሳሪያዎችን እንደ ሞርታር፣ ዲሽቃ እና ፒኬኤም በመጠቀም በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየካሄዱት ያሉት ጦረነት በጣም ከባድ እና የከፋ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

እነዚህ ፅነፈኛ የአማራ ታጣቂ የጥፋት ኃየሎች አሁንም ከባድ የጦር መሳሪያዎችን እና ተጨማሪ የሰው ኃይል በመጥራት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሰንበቴ ወረዳ አስተዳደር ጨምሮ የብልፅግና ቡድን መዋቅር፤ አብደላ ሼክ አሂመድ፣ ኡመር ሼኪቻ እና ሰኢድ አልዪ የተባሉት ግለሰቦች ከእነዚህ ፅንፈኛ የአማራ ፋኖ ታጣቂዎች ጋር በመሆን ወይም በመተባበር ሕብረተሰቡ በእነዚህ ፅንፈኛ የአማራ የጥፋት ኃይሎች እንዲገደል እና እንዲጨፈጨፍ እያደረጉ ነው። ይህም በእጅ አዙር ውስጥ ውስጡን ሕዝቡ ላይ ሴራ እየሰሩ እንዳሉ ሲያመላክት ከዚህ ድርጊታቸው እና ከጠላትነት ስራም እንዲታቀቡ የሰሜን ኦሮሚያ፣ ወሎ ነዋሪዎች አስገንዝበዋል።

የኦሮሞ ሕዝብ እራሱን ነፃ ለማውጣት ትግል ዉስጥ የገባው መሰል እኩይ ተግባራትን ከአያት ቅድመ አያቱ በወረሰው መሬት ላይ ወረራ ከሚያካሂዱት ፅንፈኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመላቀቅ ነው።

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading