ሚያዚያ 5/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በፋሺስቱ አብይ አህመድ የሚመራዉ የኢምፓየሪትዋ ሰራዊት የኦሮሞን ሕዝብ ለማስቃየት የተቋቋመ ቡድን ሙሆኑን ከእለት ወደ እለት በተግባር እያሳየ ነው። በዚህም ጥቃት የደረሰባቸው፣ ቤተሰብቻቸውን ብቻም ሳይሆን በወረዳው የሚኖሩትን ማህበረሰብ ሁሉ ሰላምና መረጋጋትን በመከልከል ላይ ናቸው። ከመኖሪያ ቤታቸውም አልፈው ስራ በሚሰሩበት ቦታ በማደን መግደል፣ ማሰር፣ ንብረታቸውን ከማዉደም እና ከመዝረፍ ጎን ለጎን ከባድ ድብደባን በመፈጸም አካለ ጎዶሎ በማድርግ ላይም ይገኛሉ።
በዚሁ መሰረት በቡኖ በደሌ ዞን ጨዋቃ ወረዳ በቡርቃ በረካ ቀበሌ ዉስጥ መጋቢት 13/2024 አዴ ሃስና አሒመድኑር የአንድ ልጅ እናት የሆነችዉን ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አለሽ በማለት ከፍተኛ ድብደባ ካደረሱባት በኋላ ወደ ጨዋቃ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ወስደው እንዳሰሯት ምንጮቻችን ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልጸዋል ።
አዴ ሃስና አሒመድኑር በአብይ አህመድ ማፊያ ሰራዊት ሃይል በተፈጸመባት ድብደባ ምክንያት በጽኑ ተጎድታ እንዳለች ሲገለጽ፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ድረስ ያለምንም ህክምና ታስራ እንዳለች ጨምረው ገልጸዋል። በተጨማሪም በእህቷ ሃንጋቱ አሒመድኑር እና ኣባታቸው ኦቦ አሒመድኑር አሊ ላይም ከባድ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ታውቋል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ ምንም አይነት ህክምና እንዳያገኙ ትዕዛዝ የሚሰጥ ኢ-ሰብዓዊነትን የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
