• Mon. Sep 14th, 2026

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የደቡብ ምሥራቅ ዞን አዳዲስ የነጻነት ሰራዊት አባሎችን አሰልጥኖ በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል

Apr 9, 2024

ሚያዚያ 9/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተንሰራፋውን ባርነት ከስሩ ለመንቀልና መላው የኦሮሞን ህዝብ ነፃነት ለማጎናፀፍ እልህ አስጨራሽ ትግል እያካሄደ በሚገኝበት በአሁኑ ጊዜ አዳዲስ ዕጩ ተዋጊዎችን በመቀበል አሰልጥኖ በማስመረቅ ስምሪት መስጠቱን እንደቀጠለ ነው።

በዚህ መሰረት በደቡብ ምሥራቅ ዞን ላይ የሚንቀሳቀሰው ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የፖለቲካ ፕርግራምና መመሪያ መሰረት ለዕጩ ተዋጊዎቹ የኦሮሞ ታሪክና ወቅታዊ የኢምፓየሪቱን መሰረታዊ ሁኔታ ትምህርት እንዲሁም ልዩ ልዩ ወታደራዊ ስልጠና ተሰጥቶዋቸዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እነዚህንም ተመራቂዎች “የጀግኖች ዱካ” በሚል ስያሜ መጋቢት 19/2024 ምርቃታቸው የተካሄደ ሲሆን በምረቃው ላይም የደቡብ ምሥራቅ ዞን ጦር አዛዥ የሆኑት ጃል ሰባኢፍ ገልጎ ተገኝተው ለተመራቂዎቹም “እንኳን አደረሳችሁ” ካሉ በኋላ የሚከተለውን ብለዋል፦

“የብልፅግናው ቡድን በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በድል አድራጊነት የምንወጣው ጠንካራ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሲኖረን ብቻ ነው።” ካሉ በኃላ በመቀጠል;

“ስለዚህ እናንተ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሆናችሁ የምትሰማሩት የታጋይን ስነስርዓት ተላብሳችሁ ለጠላታችሁ እሳት በመሆን ለነፃነት ትግሉም በቁርጠኝነት መስራት ይኖርባችሁዋል።” ብለው አስገንዝበዋል።

“ይህ ወቅት ህዝባችን በብዙ ቦታ እንደ ቅጠል እየረገፈ ያለበት ሁኔታ ውስጥ ስለሆን በርትተን ታግለን ትግላችንን ማስፋት እንዲሁም ትግሉን በድል ለመዝጋት ህዝቡ ከጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር እንዲቆም” በማለት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።

ዕጩ ምሩቃኖችም ስልጠናቸውን ጨርሰው የተመረቁት የተለያዩ የሰራዊቱ አዛዦችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ሲሆን በዕለቱም ወታደራዊ ትርዒቶችን አሳይተው ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኃላ ስምሪት ተቀብለው መሸኘታቸው ታውቋል።

ለሕዝባቸዉ ነፃነት ያለቻቸዉን ብርቅዬና ተተኪ የሌላት ህይወታቸዉን ለመስጠት ለወሰኑት ለጋ ወጣቶች ክብር መስጠት እና እንደ ኦሮሞ የሚፈለግብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆን እንዳለብን አንዘንጋ።

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading