ሚያዚያ 11/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
መጋቢት 22/2024 በምዕራብ አርሲ ዞን፣ በገደብ አሳሳ ወረዳ፣ ፉጮ ካካ ቀበሌ የፋሺስት አብይ ታጣቂ ቡድኖች 28 የገበሬ ቤቶችን ከነንብረታቸው አቃጥለዉ ማጓጓዝ የሚችሉትን ንብረት ደግሞ ዘርፈው ሄደዋል። በዚህም ምክንያት የዚህ እኩይ ተግባር ሰለባ የሆኑት ህዝቦቻችን መጠለያ የለንም፣ ልብስ የለንም ምግብ የለንም የሰውን እጅ እያየን ነው ብለው ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹም አክለው በኦሮሞ ስም የሚነግዱት ኦሮሞ ነን ባዮች እና ስልጣን የያዙት የፋሺስት አብይ አህመድ ቡድኖች፣ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጽሙት እኩይ ተግባር በኢምፓየሪትዋ ታሪክ ዉስጥ ቀድመው የነበሩት አምባገነን መንግስታት እንኳን ተፈፅሞ የማያውቅ እና ሁኔታውን እንዳንገሸገሻችዉም ገልጸዋል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት እና ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
