• Fri. May 22nd, 2026

የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር የነበሩት ጃል በቴ ኡርጌሳ ካረፉበት ሆቴል በፋሺስት አቢይ አህመድ ገዳይ ቡድን ተወስደው ተገደሉ

Apr 12, 2024

ሚያዚያ 11, 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በአብይ አህመድ የሚመራው የገዳይ ቡድን እና “የሰላም ኮሚቴ (ኮሬ ነጌኛ)” ተብሎ የተሰየመው የኦሮሞ የፖለቲካ አመራሮችን እና ምሁራንን በድብቅ መግደል በመቀጠል የኦነግን የፖለቲካ ኦፊሰርን ጃል በቴ ኡርጌሳን ገድሏል።

ሚያዚያ 9/2024 በምሥራቅ ሸገር ዞን መቂ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ልዩ ስሙ መርፈታ ግሪሳ በተባለ ቦታ ቀበሌ 03 ውስጥ ጃል በቴ ኡርጌሳ ቡላ የተባሉትን ከለሊቱ 3:00 ሰዓት አከባቢ በስድስት ጥይት ደብድበው መገደላቸውን በከተማው ያሉት ምንጮቻችን ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።

ጃል በቴ ኡርጌሳ ፊንፊኔ ከተማ የሚኖሩ ሲሆን ባለፈው ሰኞ ሚያዚያ 8/2024 ከፊንፊኔ ወደ መቂ የሄዱ ሲሆን ኖክ አከባቢ የሚገኝ ሆቱል ቤት በመያዝ ያድሩ ነበረ።

ኦነግ የሰላማዊ ትግል መንገድን አምኖ በመቀበል በሰላማዊ መንገድ ትግሉን ለማካሄድ መስከረም 15/2018 ወደ ኢምፓየሪቱ በመመለስ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመመዝገብ የፖለቲካ እንቅስቃሴውን በይፋ ሲያካሂድ እንደነብረና ጃል በቴ ኡርጌሳም የዚሁ ድርጅት የፖለቲካ ኦፊሰር እንደነበሩ የሚታወስ ነው። ጃል በቴ ኡርጌሳም የድርጅቱን የኦነግን አቋም በማራመድ ላይ እንዳሉ በተለያዩ ጊዜያት አስረው ሲያሰቃዩዋቸው ከቆዩ በኋላ በከፍተኛ ደረጃ በመታመማቸው ከእስር እንዲፈቱ ቢደረግም፣ ባለፈው ወር አንድ የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ቃለ መጠይቅ በሚያደረጉበት ጊዜ የፖለቲካ ሴራ እያሴራችሁ ነው በሚል የሀሰት ወንጀል እንደገና እንዲታሰሩ ተደርጎ ከሳምንታት እንግልት በኋላ ፈትተዋቸል።

ይህ አልበቃ ብሎት ፋሺስት አብይ አህመድ የሂትለር ጌስታፖ(Gestapo)” መሰል የግድያና የአፈና ቡድን “የሰላም ኮሚቴ (ኮሬ ነጌኛ)” በሚል ስም በማዋቀር፣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የወሰኑትን ጃል በቴ ኡርጌሳን የምርጫ ሰሉ ታጋዮችና ሌሎች ንጹሃን ኦሮሞዎችን ያላንዳች ርህራሄ ህይወታቸውን በመቅጠፍ ላይ ይገኛል። የፋሺስቱ አብይ አህመድ የማፍያ ገዳይ ቡድን የከረዩ አባ ገዳዎችን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎችን በስውር ግድያ የኤምፓየሪትዋን እድሜ ለማርዘም እየቃጣው ነው።

ይኸው የፋሺስት አብይ አህመድ ቡድን በኢምፓየሪትዋ ውስጥ ከሚተገብረው የሽብር ግድያዎችም አልፎ በጎረቤት ሐገሮችም ውስጥ ለመተግበር ዕቅድ እንዳለው የቀድሞዉ የአብይ የደህንነት አማካሪ የነበሩት አቶ ሲሳይ ቶላ ተናግረው እንደነበረ ይታወሳል። የጃል በቴ ኡርጌሳ የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ መጋቢት 11/2024 ቤተሰቦቹ በተገኙበት እንደሚፈጸምም ታውቋል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”v

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading