• Wed. Mar 11th, 2026

የጽንፈኛው የአማራ ፋኖ ታጣቂዎች በሰሜን ኦሮሚያ ወሎ ዞን አንድ ወጣት ከመኪና በማውረድ በሳንጃ ማረዳቸው ተሰማ

Apr 9, 2024

ሚያዚያ 9/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ጽንፈኛው የአማራ ታጣቂ ኃይል በፋሺስት አብይአህመድ ብልፅግና ድጋፍ አደረጃጀታቸውን በማጠናከር የዘር ማጥፋት ዘመቻ በኦሮሞ ህዝብ ላይ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች እና በወሎ ሰሜን ኦሮሚያ እያካሄዱ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት የበርካታ ንጹሃን ኦሮሞዎች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታእየጠፋ፣ ንብረታቸው እየተዘረፈ፣ መኖሪያ ቤታቸው ከነንብረቱ እየተቃጠለ ስለሆነ ህዝቡ ለተለያዩ ከባድ ችግሮች እየተጋለጠ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎአል።

የጽንፈኛው አማራ ታጣቂ የቀድሞውን ኮሎኒያል ስርዓት ለመመለስ አላማቸዉ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት በወሎ ዞን ሀርጡማ ፉርሴ ወረዳ በመንገድ ላይ በመኪናና በእግር በሚጓዙት ኦሮሞዎች ላይ በደፈጣ ጥቃት በመክፈት አሰቃቂ ግድያ እና ዘረፋ እያካሄዱ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዉልናል።

በዚሁ መሠረት መጋቢት 28/2024 ጽንፈኛው የአማራ ታጣቂ ቡድን እራሱን አማራ ፋኖ ብሎ የሚጠራው አድፍጦ በነበረበት ልዩ ስሙ መገንጣ ፉርሴ በተባለ ቦታ በጫት ንግድ እራሱንና ቤተሰቡን የሚረዳዉን ወጣት ከጨፋ ሮቢት ወደ ሰንበቴ እየሄደ ሳለ ከመኪና ላይ በማውረድ ገንዘብ እና በእጁ የያዘዉን ንብረት ከዘረፉ በኋላበሳንጃ አርደዉ ከገደሉት በኃላ ሬሳውን መሬት ላይ ሲጎትቱ ውለው ሲመሽ አስፋልት ላይ ጥለውት ሕዝቡ ክቡር ሰውነቱን አንስቶ እንዳይቀብር ማስጠንቀቃቸዉን ምንጮቻችን ነግረዉና።

የብልጽግናው ማፍያ ቡድን የኦሮሞ ንጹሃን በጽንፈኛው አማራ ታጣቂ ፋኖ እየተገዱሉ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት መከላከል ሲገባውና ግድያዉንም ማስቆም ግዴታው መሆኑ ቢታወቅም “ፋኖ ሳይሆን አገር ለመያዝ እየተንቀሳቀሰ ያለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነው” በማለት በሰሜን ኦሮሚያ ወሎ ውስጥ በሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ላይ ጠንካራ ዘመቻ ለማድረግ በጠሩት ስብሰባ ላይ ገልጸዋል። ለዚህም ምላሽ ህዝቡ በስም እራሱን የኦሮሞ መንግስት ነኝ የሚለዉ በስውር የሚዘርፈን እና የሚያዘርፈን፣ የሚጨፈጭፈንና የሚያስጨፈጭፈንን ሃይል የሰላም አስከባሪ እና ለኦሮሞ ሕዝብ የቆመ ነው ለማለት አንድፍርም በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading