ግንቦት 1፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የአማራው ጽንፈኛ ታጣቂዎች አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በእሱም እገዛ በትጥቅ እና አደረጃጀት ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከሩ ይገኛሉ። የዘር ማጽዳት ዘመቻቸውንም ከፋሺስት አቢይ ጦር፣ የአማራው እና የኦሮሚያው የብልፅግና ቡድን ጋር በመቀናጀት የአማራ ክልል አጎራባች የሆኑትን የኦሮሚያ ክልል ዞኖች እና በሰሜን ኦሮሚያ፣ ወሎ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርጉትን የጦር ወንጀል ከምን ጊዜው በላይ እያፋፋሙት ይገኛሉ።
በሀርጡሜ ፉርሲ እና ጨፌ ራንዶዬ ወረዳዎች
ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዚያ 1፣ 2024 ድረስ ጽንፈኛው የአማራ ፋኖ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በሀርጡሜ ፉርሲ እና ጨፌ ራንዶዬ ወረዳዎች በከፈተው ጦርነት ከበባድ የጦር መሳሪያዎችን ዲሽቃንም ጨምሮ ሲጠቀሙ ዉለዋል። በዚህም ጦርነት ከ12 ሰዎች በላይ ሲቆስሉ ከቆሰሉትም ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልፀዋል። ከዚህም በላይ በዚህ ጥቃት በርካታ የሕዝባችን ቤት እና ንብረት በነዚህ ታጣቂዎች መቃጠሉን እና ማጓጓዝ የሚችሉትንም ንብረት መዝረፋቸዉን ነዋሪዎቹ አሳውቀውናል።
ከቆሰሉትም ንጹሃን ኦሮሞዎች ስማቸውን ያገኘነው፦
- አዴ ሀሊማ ሞሐመድ አደም ከዲዶ ቀበሌ፣
- አዴ ጠይባ ኡመር ቢላሁ ከጪሪ ቀበሌ፣
- ኦቦ አሊዪ ኡሙር ከጃራ ቀበሌ፣
- ኦቦ ሀሰን መሐመድ አልዩ ከዲዶ ቀበሌ፣
- ኦቦ አህመድ ሼክ ኡመር ከዲዶ ቀበሌ፣
- ኦቦ አልዪ ሙሴ ከዲዶ ቀበሌ፣
- ኦቦ አሊዪ ሀሰን ሳሊ ከዲዶ ቀበሌ፣
- ኦቦ ጎንፌ ሀሰን ከዲምቱ ቀበሌ እና
- ኦቦ አሂመዲዩ ከዲምቱ ቀበሌ ናቸው።
ጽንፈኞቹ የአማራ ኃይሎች በብልፅግናው አንጃ ተደግፈው የአባቶቻቸው የምኒልክን ስርዓት ከግብ ለማድረስ እና የኦሮሞን ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከዕለት ወደ ዕለት የተለያዩ አጀንዳዎችን በመፍጠር ግድያን፣ ንብረት ዘረፋና ከነንብረቱ ቤትን በማቃጠል በኦሮሞ ህዝብ ላይ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸሙ ይገኛሉ።
ዳዋ ጨፋ ወረዳ
ከሚያዚያ 16፣ 9:00 ሰዓት እስከ ሚያዚያ 18፣ 2024 በተረፍ እና ኤሌሞ ቀበሌዎች እንዲሁም በኡራኔ እረኞች ከብት በሚያግዱበት ኡጉሎ እና ራንዶዬ በሚባሉ አካባቢዎች ጽንፈኛው የአማራ ፋኖ ቡድን ባደረጉት የጦር ወረራ ብዙ ንጹሃን ኦሮሞዎችን ገድለዋል ብዙዎችንም አቁስለዋል። በዚህም ወረራ ማጓጓዝ የሚችሉትን ንብረት ዘርፈው የተረፈውን ደግሞ ከቤቶቻቸው ጋር በእሳት አውድመዋል።
ከተገደሉት መካከል አራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ስማቸውን ለጊዜው ያገኘው፦
- መሐመድ አህመድ ከቃሎ ከተማ፣
- ሁቢ ከቃሎ ከተማ፣
- ሰዒድ ገርቢ እና
- ሰዒድ ሃሰን ናቸው።
ሚያዚያ 18፣ 2024 ኤሌሞ እና ፋጮ ቀበሌ ውስጥ ጽንፈኛው እና በፋሺስት አቢይ ብልፅግና ቡድን የሚደገፉት ፋኖ ቤት ንብረት ከማቃጠላቸውም በላይ ስድስት ኦሮሞዎችን አፍነው ወስደው ያሉበትን ማግኘት አለመቻላቸው ምንጮቻችን ነግረዉናል።
ከሚሴ ከተማ
የምኒሊክን ስርዓትን ለመመለስ አላማ ያላቸው የአማራ ክልል ብልፅግና ባለስልጣኖች ጽንፈኛውን ፋኖ ቡድን በተለያየ ስልት ወረራውን እንዲያሳካ እየረዱት መሆኑንም በግልፅ እየታየ ነው። ይኸውም 270 የሚሆኑ የጽንፈኛው የአማራ ፋኖ የክልሉን ሚሊሻ ዩኒፎርም አልብሰው ወደ ከሚሴ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ መላካቸውን እዚያም ከዉይይታቸው በኋላ ወደ ሕዝቡ ተመልሰው ተኩስ መክፈታቸውን ምንጮቻችን አሳውቀዉናል። .
ይህም የወረራ ጦርነት ለቀናቶች ተካሂዶዋል። የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን ጽንፈኛውን ፋኖ ከማስታጠቅ፣ ከሗላ በኩል ሆኖ ከፋኖ ጥቃት የሚያፈገፍጉትን ኦሮሞችን ከመግደል አልፈዉም አሁን ደግሞ አብረው ”አንዴት ኦሮሞን ማጥፋት እንችላለን?” ብለው ፍኖተ ጥቃታቸውንም ነድፈው ስራ ላይ እያዋሉት ይገኛሉ። የኢፓየሪትዋንም ሆነ የአለም ሕግጋትን እየጣሰ ያለው የፋሺት አብይ ብልፅግና ቡድን በሰሜን ኦሮሚያ የሚገኘውን ሕዝባችንን ከብቦ ለመጨረስ የተዝጋጀም ለመሆኑ እራሱን እንኳን የሚከላከልብትን ዱላ ሳይቀር በየመንገዱ ከሚያገኛቸው ሁሉ እየሰበሰበ በአንፃሩ ደግሞ ፅንፈኛ ቡድኑን ከባባድ የጦር ሜዳ መሳሪያዎችን እያስታጠቀ ይገኛል።
በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም እና ሁልላችሁም አደብ ብትገዙ ጥሩ ነው እንላለን።
