ግንቦት 11፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በአምባገነኑ ኮሎኔል አብይ አህመድ የሚመራው ብልጽግና ቡድን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በኦሮሚያ ውስጥም ሆነ በሌሎች ክልሎች (በውሎ (አማራ ክልል)) እና (በመተክል (ቤኒሻንጉል ግሙዝ ክልል)) ዉስጥ እየፈፀሙ ያሉትን ዘግናኝ ድርጊቶች ወደ ዘር ማጥፋት ደረጃ በመድረሱ ኦሮሞ እንደ ሕዝብ መኖር መቻሉንም ጥርጣሬ ውስጥ እየከተተው ይገኛል።
በዚህም ሁኔታ ከመጋቢት 22፣ 2024 ጀምረው በተከታታይ ቀናት በምዕራብ አርሲ፣ በገደብ አሳሳ ወረዳ፣ በጮፊራ ሻሼ እና ጮፊራ ሁሉቆ ቀበሌዎች ውስጥ 32 የኦሮሞ ቤቶችን በማፍያው ብልፅግና ጦር መቃጠሉን ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
ቤት ከሙሉ ንብረታቸው ጋር የተቃጠለባቸው፦
- ሙክታር ሐጂ ከዲር 1 ቤት፣
- ጀማል ሐጂ ከዲር 5 ቤቶች፣
- ሙዲ ቡርቃ 6 ቤቶች፣
- ገለቶም ሁሴን 1 ቤት፣
- አቡና በdhaaሶ 2ቤቶች፣
- ራዪዮ ሆራቶ 1 ቤት፣
- በከር ሌንጂሶ 1 ቤት፣
- ጉደታ ሌንጂሶ 1 ቤት፣
- በdhaaሶ ፋኖ 2 ቤቶች፣
- አብደላ ፋኖ 6 ቤቶች፣
- አማኖ በdhaaሶ 2 ቤቶች፣
- አብዱረማን ቡርቃ 2 ቤቶች፣ እና
- አሺም ገለቶ 2 ቤቶች ናቸው።
ሁለት ሰዎች ስማቸውን ለጊዜው አቢኦ ያልደረሰው የተገደሉ ቢሆንም የኦቦ ሙዲ ቡርቃ ወንድሞች መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሩዎች ጨምረው ተናገረዋል።
የብለፅግና ካድሬዎች እና ጆሮ ጠቢዎች በመሆን ይህን የግፍ ስራ በግንባር ቀደምትነት እያከናወኑ ያሉት፦
- ሞሐመድ ከዲር የወረዳው አስተዳዳሪ፣
- ከዲር ሁሴን የወረዳው የፀጥታ ጉዳይ፣
- ጀማል ገለቱ፣ እና
- ጀማል አብዱሮ እንደሆኑም ታውቋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት፣ እና ንጹሃን ኦሮሞን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ለማዘዝ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
