• Sat. Aug 29th, 2026

የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እገዳ ጥሪ (ከየኦሮሞ ነፃነት ቄሮ የተሰጠ መግለጫ!)

Sep 2, 2024

የኦሮሞ ህዝብ ቄሮና ቀሬ በጠሩት የሕዝብ ንቅናቄዎች በተለያየ ረድፍ ሲሳተፉ ቆይተዋል። የኦሮሞ ህዝብ እምቢተኝነት በማየሉ በኢምፓየሪቱ የሚኖሩ ህዝቦች የትግሉ እጋር ሆነው በመነሳታቸው የኢህአዴግ ስርዓት መስራቹ ህውሓት መዳከሙ ገብቶት ወደ መቀሌ መሄድን በመምረጥ የቄሮ እና ቀሬ የህዝብ እምቢተኝነት ንቅናቄ በድል ተጠናቀቀ። ሆኖም ግን፣ ድሉ በወያኔ በሰለጠኑ ጀሌዎች ተጠልፎ፣ ተጠብቆ የነበረው የነፃነት ጮራ ደብዝዞ፣ ወደሌላ የጭቆና ስርዓት ተጠናክሮ የንብረት ውድመትን እና የንፁሃን ህይወት እልቂትን በኦሮሞ ምድር ላይ ማስተናገድ በስፋት ቀጠለ።

በኦሮሞ ህዝብ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የብልፅግና የጦር ቡድን ባቋቋመው እና በብልፅግና በሚደግፈው የአማራ አክራሪ ቡድን በመሆኑ፣ የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ ቁጭ ብሎ ማየት ስላልቻለ፣ በተለያየ ወቅት የህዝቡን እምቢተኝነት ሲያውጅ እና ሲተገብር ቆይቷል። ዛሬም በኦሮሞ ቀዬ ላይ እየተካሄደ ያለውን የጅምላ ግድያ፣ እስር፣ ዝሪፊያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የቤትና ንብረት ቃጠሎ እና መፈናቀል ለማስቆም የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ በቁርጠኝነት ለመምራት ወስኗል።

ወራሪው የብልፅግና ጦር ዛሬ በኦሮሚያ የኦሮሞን ቀዬ በከባድ የጦር መሳሪያዎች፥ በ Zu-23፣ ሞርታር፣ ታንክ እና በድሮን እየደበደበ ሲሆን፣ በሰዎች ህይወት እና በንበረት ላይ የሚያደርሰው ከፍተኛ ጉዳትም እየተመዘገበ ይገኛል።

በዚህች ኢምፓየር ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ የመኖር ህልውናው ደብዝዞ፣ በጅምላም የፓለቲካ አመለካከቱ ተለይቶ እየተረሸነ፣ የሐዘን ማቅ ለብሷል፤ ስለዚህም ነው የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ የህዝብ እምቢተኝነት ንቅናቄን ማጠናከር ትክክለኛ ምርጫ ነው ብሎ የሚያምነው።

የብልፅግናው ፓርቲ የሰላሙን መንገድ ሁሉ የዘጋው እራሱ ሆኖ ሳለ፣ በተጨባጭ በምድር ላይ የኦሮሞን ቀዬ በጦርነት እየናጠ፣ ቤት ንብረት በእሳት እያጋየ፣ በመገናኛ ብዙሃኖቹ ስለ ሰላምና እርቅ እየስበከ፣ በሌላ በኩል የህብረተሰቡን ሰላም ነስቶ፣ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ ሲባል የኦሮሞ ህዝብ መከታ ለምምሰል ህብረተሰቡ ሰላም እንዲወርድለት ጠየቀ ብሎ እያጭበረበረ ይገኛል። ስለሆነም፣ መፍትሄው ተቃውሞውን ማጠናከር እና ህዝባችንን መብቱን ለማጎናፅፍ፣ የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እቀባ አውጀናል።

ይህ የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እቀባ ጥሪ እንደ ኢምፓየርዋ አቆጣጠር ዓርብ ጳጉሜ 1፣ 2016 ጀምሮ፣ እስከ 2017 የሀርሰዲ እሬቻ በዓል ቀን ድረስ የሚቆይ ይሆናል። ይህም ማለት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከዓርብ መስከረም 6፣ 2024 ጀምሮ እስከ 2024 የሀርሰዲ እሬቻ በዓል ቀን ድረስ የሚቆይ ይሆናል። (ለኢሬቻ በዓል ልዩ ፍቃድ እና የአፈፃፀም መመሪያውም በዚሁ ጥሪ ውስጥ ተገልጿል)።

የኦሮሞ ህዝብ እራሱን ከጥፋት ለማዳን እና የተሰነዘረብንን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማክሸፍ የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ በጠራው ህዝባዊ እምቢተኝነት ጥሪ ሁላችንም የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ግዴታችንን መወጣት ወሳኝነት አለው።

ይህ የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እገዳ ጥሪ ለኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በኦሮሚያ ውስጥ ለምትኖሩ እና ተመሳሳይ እጣ ፋንታ ያለን ብሔር ብሔረስቦች፣ በብልፅግና ስርዓት ጭቆና እየማቀቃቹ ያላችሁ እና የብልፅግና ቡድን ለኢምፖየሪቷ ህዝቦች አይበጅም የሚል እምነት ያላችሁ በሙሉ በገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እገዳ ላይ እንድትሳተፋ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

  1. በዚህ የእቀባ ጥሪ
     በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ መንገዶች ሁላ ዝግ ይሆናሉ።
     አዲስ አበባን (ፊንፍኔን) የሚያገናኙ መንገዶች ሁላ ዝግ ይሆናሉ።
     ኦሮሚያን ከሌሎች አጎራባች ክልሎች (ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ሲዳማ፣ የደቡበብ ህዝቦች፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ አፋር) ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ሁላ ዝግ ይሆናሉ።
     ከሞያሌ ኬንያ የሚያገናኘው መንገድ ዝግ ይሆናል።
     የመኪና፣ የሞተር ብስክሌት/ዶቅዶቄ እና የባጃጅ እንቅስቃሴ አይኖርም።
     የመነግስት ስራ የለም።
     ባንክ ቤቶች ዝግ ናቸው።
     ገበያ አይኖርም።
     ሱቆች (የገበያ አደራሾች) ዝግ ናቸው።
     ሆቴሎች ዝግ ናቸው
     የተለያዩ የእምቢተኝነት ምልክቶችን (እጆችን በማጣመር፣ ትግል እደሚቀጥል ማሳያ እና ጥቁር ልብስ መልበስን) ይበረታታሉ።
     በተለይም የአትክልት፣ ፍራፍራ፣ የቀንድ ከብት፣ ፍየል፣ በግ፣ መዓድን፣ እህል እና ሸቀጣሸቀጥ ወደ እና ከፊንፊኔ ማጓጓዝ በእነዚህ የእቀባ ቀናቶች ክልክል ናቸው።
  2. ልዩ ፍቃድ ያላቸው ጉዳዮች
     የኢሬቻ በዓል ለማክበር በመኪና የሚንቀሳቀሱ ሰዎች (በኢሬቻ ሳምንት ውስጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች የኢሬቻ በዓል ለማክበር የሚንቀሳቀሱ ተጓዦችን ለማጓጓዝ ክፍት ነው። ነገር ግን ከተፈቀደው አላማ ውጪ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ክልክል ነው።)
     በሽተኛን እና ወላድን/ነፍሰ-ጡርን የሚያጓጉዝ አምቡላንስ (ወታደር የማይጭን አና ለተመደቡበት ስራ ብቻ የሚያገለግሉ መሆን አለባቸው)
     ይህንን የህዝብ እንብተኝነት ለመዘገብ የሚንቀሳቀሱ የውጪ እና የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች ካሉ የተፈቀደላቸው ይሆናል።

ይህ የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እቀባ ጥሪ የኦሮሞ ማህበረሰብ በሙሉ ባሳተፈ መልኩ እንዲካሄድ መልዕክተታችንን ስናስተላልፍ፣ አሽከርካሪዎች እና ባለሀብቶች ለጊዜያዊ ጥቅም ብላችሁ ይህንን የአድማ መመሪያ ከመጣስ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን።

የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ የህዝብ እምቢተኝነት ትግልን ሊከተል በሚገባው ስነምግባር በመመራት በስረዓቱ ላይ በሚደረገው እምቢተኝነት ላይ ብቻ ትኩርት ሰጥታችሁ እንድትንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ ኮሚቴ ያሳስባል።

ህዝባችህን ዝምታን የመጨረሻው ሊያደርግ ይገባል። ዝም ማለት፣ ምን አገባኝ እና ሌላ ሰው እንዲታገልልን መጠበቅ ይበቃል። የኦሮሞ ደም ከዚህ በላይ እንዳይፈስ፣ አጥንቱ እንዳይከሰከስ፣ የመቶ ሺዎች ህይወት እንዳያልፍ፣ እና በመቶ ሺዎች ወደ እስር ቤት እንዳይጋዝና እንዳይሰቃይ ዛሬ በአንድነት ተነስተን መታገል አለብን።

ለዚህ የህዝብ እምቢተኝነት ህዝባችን አስቀድሞ እንዲዘጋጅ እና በተለያዩ ምክንያቶች ከቤቱ ውጥቶ መንገድ ላይ የሚገኝ፣ በተሰጠው ግዜ ወደ ቀዪው እንዲሰበሰብ አጥብቀን እናሳስባለን።

ነፃነትን በነፃ የሚሰጥ ጨቋኝ ስለሌለ የህዝብ እምቢተኝነትን ማጠናከር የኦሮሙማ ግዴታ ነው!

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ

መስከረም 2፣ 2024

ፊንፍኔ፣ ኦሮሚያ

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading