መስከረም 3፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮሞ ልጆችን ይዞ መሰወር፣ ደብድቦ አካለ ስንኩላን ማድረግ፣ አስሮ ማሰቃየት፣ አረመኔያዊ መስፈርትን ተከትሎ መግደል፣ ከገደለም በኋላ ወደ ዱር አራዊት መጣልን ተክኖ ከስድስት አመት በላይ ኦሮሚያን እና ንፁሃን ኦሮሞዎችን የሚያሸብረው በፋሺስት አብይ የሚመራው ብልፅግና ቡድን አሁንም እጁን በንፁሃን ደም ማጨቅየቱን ቀጥሎበታል።
ቄለም ወለጋ ዞን፣ ሳዮ ወረዳ
በሚንኮ ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩ ሰባት የተከበሩ እና በኦሮሞ ህብረተሰብ ውስጥ የሚወደዱ አዛውንቶችን ሐምሌ 29፣ 2024 ይዘው ወደ እስር ቤት አጉረዋቸዋል። ስማቸውም፦
- ኦቦ አየሎ ሱሌማን፣
- ኦቦ ጊርማ አየላ፣
- ኦቦ ቤካ ቀኖ፣
- ኦቦ ቡዛዮ ኢተፋ፣
- ኦቦ አቦማ መሳዲ፣
- ኦቦ ዜኑ ፋርሲ እና
- ኦቦ ለቲሞ ሻፊ የሚባላሉ።
እነዚህም አዛውንቶች የቤተሰብ ኃላፊዎች እና ለአከባቢያቸው ተቆርቋሪ ከመሆናቸው ውጪ በፖለቲካ ውስጥ ምንም ተሳትፎ የሌላቻው እንደነበሩ ነገር ግን የፋሺስት ብልፅግና ቡድኑ በሃሰት “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትደግፋላችሁ” በማለት ወንጅለው በእስር ቤት ውስጥም እያሰቃዩዋቸው መሆኑን የእቢኦ ከምንጮቹ መረጃውን አግኝቷል።
ምስራቅ አርሲ መርቲ ወረዳ
ሐምሌ 30፣ 2024
- ለግዜው ስሙን ማግኘት ያልተቻለ በወተሮ ዱኖ ቀበሌ ነዋሪ የነበረው የ20 ዓመት ቄሮ፣ ቦሌ ከተማ ውስጥ የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን ምን ልትፈልግ መጣህ እዚህ ብለው ጥይት እንደ ዝናብ አርከፍክፈው ገድለውታል። ይህም ቄሮ የልጅነት እድሜውን በፋሺስት ብልፅግና እስር ቤት ውስጥ ለብዙ ዓመታት ሲያሰቃዩት የነበረና ኦሮሙማን አንፀባራቂና በኦሮሞነቱ የማይደራደርም ነበር።
በዚሁ ቀበሌ ውስጥ ይኖር የነበረውን ጀማል ሃዋሲ የተባለውን ግለሰብ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ ንብረቱን ዘርፈው፣ አንድ ድልብ ሰንጋም አርደው እንደበሉም የአካባቢው ህዝብ ለአቢኦ ገልፀዋል።
- በቡልጎታ ባዲያ ቀበሌ ውስጥ እልል አብዱሬ የተባለ ግለሰብን “ከኦነሰ ጋር ግንኙነት አለህ” በሚል የሃሰት ውንጀላ ይዘውት በእስር ቤት እያሰቃዩት ነው።
ሐምሌ 29፣ 2024
በወተሮ ዱኖ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትን አልፉ ኡሲ እና ኡሶ ጎዳና የተባሉትን ግለሰቦች የብልፅግናው ጦር ቡድን ከስራ ቦታቸው በመያዝ በእስር ቤታቸው እያሰቃዩዋቸው እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ።
ቡኖ በደሌ ዞን፣ ዳቦ ሃና ወረዳ
የጉቴ አሙማ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ኦቦ ደረጄ ገዛኝ በብልፅግናው ጦር ቡድን ሐምሌ 26፣ 2024 ተይዘው በእስር ቤት እያሰቃዩዋቸው እንደሆነ እና የታሰሩበትም ምክንያት “የአንተ ልጅ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነው።” በማለት መሆኑን ምንጮቻችን አሳውቀውናል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ፣ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
#ጨቋኙ_ኃይል_በኦነሰ_ኃይል_ይገረሰሳል!
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
