በፋሽስቱ የብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት፤ የጦር ወንጀሎችን እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመቃወም የካቲት 6፣ 2024 የገበያ ዕቀባ እና የትራንስፖርት እገዳ ዘመቻ በኦሮሞ ነፃነት ቄሮ መታወጁ ይታወሳል።
ሕዝባችን በብልፅግና ወታደራዊ ሃይሎች ከፍተኛ ዛቻና ስቃይ ቢደርስበትም አዋጁን ከኦሮሞ ነፃነት ቄሮ ጎን ሆኖ በማሳካት፣ የብልፅግናን የበሰበሰ መዋቅር ለሰላምና መረጋጋት ዋስትና ሊሆን ቀርቶ፣ በኢምፓየሪቷ ውስጥ ለሚከሰተው የብሔር ብሔረሰቦች ችግር መፍትሄ መስጠት የሚችል አካል እንዳልሆነ አሳይቷል። ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ በመንግስት ስም ህዝቡን እየዘረፉ ባሉት የዘራፊዎች ቡድን ላይ ደርሷል።
ከዚህም በላይ ‘እኔ መንግስት ነኝ’ እያለ እራሱን የሚጠራው ቡድን፣ በኢምፓየሪቷ ግዛት ውስጥ ያሉ የተጨቆኑ ብሔረሰቦችን ችግር ለመፍታት ምንም ፍላጎት የሌለው መሆኑ፣ ለህዝብ ጥያቄዎቸ ምንም ምላሽ እንደሌለው ወይም ለሕዝብ ያለው ንቀት ትልቅ መሆኑን በግልፅ አሳይቷል። ይህም ህዝቦች ተባብረው በኢምፓየሪቷ የሰፈነዉን አምባገነን ስራዓት በጋራ ከመታገል ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌላቸው አመላካች ነው።
በኦሮሞ ነፃነት ቄሮ የታወጀው የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እገዳ ሙሉ በሙሉ የተሳካ ሲሆን፣ አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ እንዲችል፣ የኢሬቻ እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉዞ እንዳይስተጓጎል አዋጁ የካቲት 25፣ 2024 ማታ ከ12:00 ሰአት ጀምሮ መነሳቱ እንዲታወቅ እናሳስባለን።
ይህን የገበያ አድማ እና የትራንስፖርት እገዳ መግለጫ እንዲሳካ ጉልህ ተሳትፎ ያበረከታችሁ ምስጋናችን የላቀ መሆኑን እየገለፅን፣ ይህ አዋጅ ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ የህዝቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ የሚፈልግ አካል ካለ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንድታደርጉ እና የሕዝቡን የተረጋጋና ሰላማዊ እንቅስቃሴ የእገዳው አዋጅ ከመውጣቱ በፊት ወደነበረበት እንዲመለስ የበኩላችሁን አስተዋፆኦ እንድታደርጉ እናስገነዝባለን።
የኦሮሞ ነጻነት ቄሮ ያስተላለፈው የገብያ ማዕቀብ እና የትራንስፖርት እገዳ መነሳቱን በአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) ቴሌቭዥን፣ ራዲዮ፣ ፌስ ቡክ፣ ትዊተር… ወዘተ እንድትከታተሉ እናሳስባለን።
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ
መስከረም 25፣ 2024
ፊንፊኔ፣ ኦሮሚያ
