• Fri. May 15th, 2026

በአርሲ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰው እልቂት (የኦነግ-ኦነሠ መግለጫ)

Mar 3, 2026


አብይ አህመድ ስልጣን ላይ መንጠልጠያ ዋና መርህ አድርጎ ከተያያዛው ስልቶች ዋነኛው፣ የሀገሪቱን ህዝቦች እና ተቃዋሚ ሃይሎች እርስ በርስ ማጋጨት እና በፍርስራሹ መሃከል ጎልቶ መውጣት እንደሆነ ይታወቃል። ባለፉት ስምንት ዓመታት፣ “ፍቅር”፣ “ሰላም” እና “መደመር” ተብሎ ባሸበረቁ ቋንቋዎች የተሸፈነው ይህ የመከፋፈል መርዝ የከፋ ሰብዓዊ አና ቁሳዊ ውድመትን አስከትሏል።

ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ፤ 1) አብይ ወለጋ ላይ ባደረገው ንግግር፣ የኦሮሞ ጥቅም አስጠባቂ መስሎ በመቅረብ፤ “የሰሜኑ ማህበረሰም ኦሮሞ ያገኘዉን ዕድል ሊነጥቁህ ቢላዋ ይዘው እየመጡብህ ነው” ሲል ቀስቅሷል። 2) የወልቃይት እና ራያ የምርጫ ክልሎችን አንዴ በትግራይ፣ መልሶ ከትግራይ ውጪ እንደሚካተቱ በማወጅ ቦታዎቹን ዘላቂ የአኬልዳማ ምድር ለማድረግ ሞክሯል። ይህ ሁሉ የሚደረገው፣ ተቃዋሚዎቹ ሳይዳሙ ዘውድ ማጽናት እንደማይችል ስለደመደመ ብቻ ነው።

ባለፉት ቀናት ደግሞ በአርሲ ሲርካ ወረዳ ንጹሃን የኦርቶዶክስ ተከታዮችን ባሰማራቸው ተላላኪዎቹ አስጨፍጭፏል። አላማው አንድ እና ያው ነው። ንጹሃን የኦርቶዶክስ ተከታዮችን በማስጨፍጨፍ የኦሮሞና የአማራ ሃይሎችን ማጋጨትን በማሰብ የተደረገ የድንቁርና የፖለቲካ ትንታኔ የወለደው ጭካኔ ነው።

በኦሮምያ የሚኖሩ ህዝቦች በሙሉ ዜጎቻችን፣ ወንድሞቻችን ናቸው። ማንም ይሁን፣ ከየትም ይምጣ፣ በንፁሀን ደም የሚነግድ ደመኛ፣ የዘላቂ ጥቅማችን፣ የንጹሃኑ ህዝቦቻችን አብሮነት፣ ቀንደኛ ጠላት ነው። ተቀናቃኝ አይደለም። ተቃዋሚ አይደለም። ጠላት ነው። ይህ ሰንኮፍ ከምድራችን እስኪነቀል እስከመጨረሻው እንታገለዋለን።

የ ኦነሠ ከፍተኛ ዕዝ
ማርች 2, 2026

Oromia #Ethiopia

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading