ነሐሴ 31፣ 2024 አራታ ቢዮሌሰ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽኒጋውን ቃል-ኪዳን ዘመቻ በቀጣይነት ለማሳካት የተሰማራው በምሥራቅ አርሲ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ የፋሺስት አብይ አህመድ ካምፖችን በመክበብ እረፍት እያሳጣቸው ይገኛል።
አንበሳውና አይበገሬው የኦነሰ የሚከተሉትን አኩሪ ድሎች ነሐሴ 13፣ 2024 በሶስት የተለያየ ስፍራ ውስጥ አከናውኗል።
አስኮ ወረዳ
የኦሮሞ ህዝብ መከታና አለኝታ የሆነው የኦነሰ አምባ አኖሌ ብርጌድ በጨፌ ከተማ አስተዳደር እና በቢዮ ቀበሌ ውስጥ ከቀትር በኋላ 10:45 ሰዓት ሁለቱን የብልፅግና ሰራዊት ካምፖችን በመክበብና አድፍጦ በማጥቃት እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ጦርነት አካሂዷል።
በዚህም ውጊያ 13ቱን ሲገድል፣ 11 ክፉኛ አቁስሎ እና የተረፋትም የባሩዳው ሽታ እንገፍግፎዋቸውና አስክሮዋቸው እግሬ አውጭኝ ብለው በተለያየ መንገድ ፈርጥጠዋል። ከዚህም በላይ ወታደራዊ አልባሳትን ጫማዎችንም ጭምር በመፍታት ለነፃነት ትግሉ ገቢ ከማድረጉም በላይ ሁለቱንም የጠላት ካምፖች በእሳት አጋይተው አመድ አድርገዋል።
ሮቤ ዲዳ ወረዳ
ጠንካራ አቋምና ሃቀኛ ዓላማ ያነገቡት የነdhi ገመዳ እና መደ ወላቡ ብርጌዶች በጥምር በሰዲቃ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በመሸጉትና የአብይን ስልጣን ለማቆየት ህዝባችንን ሲያስቸግሩና መከራ ሲያሳዩ በነበሩት ኃይሎች ላይ ካምፓቸው ድረስ አድፍጠው በመግባት በወሰዱት እርምጃ 23ቱን ወደ ማይመለሱበት ሲሸኙ 12ቱን ደግሞ የማይሽር ቁስል አከናንበው ሸኝተዋል።
ኦነሰ ከዚህ በላይ በተገለፁት ሁለት ወረዳዎች ውስጥ በወሰደው እርምጃ በመሳሪያ በኩል፦
- 6 AKM ጠመንጃዎችን እና
- በርካታ ግዜ ያለፈባቸው ጠመንጃዎች
ፈትተው ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርገዋል።
በዚሁ ውጊያ ህይወታቸው የተረፉ የፋሺስት ብልፅግና ወታደሮች ክፉኛ በመሸበራቸው ከካምፑ በሚሸሹበት ግዜ ልብሳቸውን ቀይረው፣ እንደ ሰላማዊ ሰው ህዝቡን በመምሰል በመንገድ ላይ ሲሄዱም እንደነበረ ታውቋል።
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!
