• Sun. Apr 26th, 2026

በሰሜን ሸገር ሰላሌ መፈናቀል እና አሰቃቂ አንገት መቅላት ቪዲዮ ላይ ኦነሠ (OLA) ባደረገው ሰፊ የምርመራ የተግኙ ጊዜያዊ ግኝቶች (ኦነግ-ኦነሠ ጋዜጣዊ መግለጫ)

Dec 1, 2024

በሰሜን ሸዋ ዞን በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ጥቃት የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በማስመልከት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሰፊ ምርመራ አድርጓል። ይህ የጋዜጣዊ መግለጫ ጊዜያዊ ግኝቶቻችንን በመሬት ላይ ያለውን እውነታ በማቅረብ እና በአገዛዙ ውስጥ ባሉ የተረጋገጡ ማስረጃዎች እና የውስጥ መረጃዎች ላይ በመመርኮዝ አጭር ትንታኔዎችን በማቅረብ ግልጽነት እንዲሰጡን ያደርጋል።

ሀ. እውነታው

1. በአካባቢው የታጠቁ ተዋናዮች ስብጥር

ከኦሮሞ ነፃ አውጭ ሠራዊት (ኦነሠ) እና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት ጎን ለጎን በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ውስጥ የሚከተሉት ሦስት ቡድኖች ይንቀሳቀሳሉ።

የደራ ፋኖ፡- ይህ ቡድን የደራ ፋኖ እያለ እራሱን የሚጠራ ቢሆንም በአብዛኛው የሚንቀሳቀሰው እንደ ሽፍታ መረብ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆችን ያነጣጠረ ነው። በአማራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው ሰፋ ያለ እና የተዋቀረው ፋኖ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእርግጠኝነት አይታወቅም። ሆኖም ግን በአለማየሁ አያሌው አማካኝነት በተቀናጀ የጥይት አቅርቦት የሚንቀሳቀስ ነው። አለማየሁ እራሱም ከደራ ከሆነው የመከላከያ አዛዡ የሌ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ወንድም ሲሆን፣ በጄኔራሉ ትዕዛዝ የሚሰራ ነው።

የታጠቁ ነዋሪዎች፡- ሁለተኛው ቡድን ኦሮሞ እና አማራ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችን ያቀፈ ሲሆን አልፎ አልፎም ማህበረሰባቸውን ከውጪ ስጋት ለመከላከል መሳሪያ የሚያነሱ ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች የተደራጀ ሚሊሻ አካል አይደሉም ነገር ግን ቤታቸውን እና ኑሯቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ ሲሉ ምላሽ የሚሰጡ ናቸው።

የመንግስት ሚሊሻ ሃይሎች፡- ሶስተኛው ቡድን በወረዳው ውስጥ የሚንቀሳቀሱ በመንግስት የሚደገፉ የሚሊሻ ሃይሎችን ያቀፈ ነው። እነዚህ ሚሊሻዎች ጸጥታን የማስከበር ኃላፊነት የተሰጣቸው ቢመስልም፣ ብዙውን ጊዜ እንደ የደራ ፋኖ ካሉ ቡድኖች ጋር ባላቸው ትብብር ምክንያት ውጥረቱን የሚያባብሱና፣ በምርመራ ስር ላለው አካባቢ አለመረጋጋት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ናቸው።

  • የሰሞኑ ጥቃቶች መነሻ

በዳራ እና በማራቤቴ ከተማ ጥቃቱ የጀመረው በሰላሌ አካባቢ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ሆነው የሚያገለግሉ ሌ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እና የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪው አቶ ከፍያለው አደሬ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ በደራ ወረዳ ከሰባት ቀበሌ ከተውጣጡ የኦሮሞ ተወላጆች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው። እነዚህ ሰባት ቀበሌዎች ገብሮ በሬሳ፣ አቡ ጎዶ፣ በሂት ከራባ፣ ሆማ ቡኒያ፣ ሆማ በሬሳ፣ ጉደቱ ገባ ሰኞ እና ሰረርኩላ ናቸው። አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆች ቀደም ሲል በመሰል ስባሰባዎች ላይ ያጋጠሟቸውን — ትጥቅ መፍታት ወይም የመንግስት ሃይሎችን በመቀላቀል የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን እንዲዋጉ የተጠየቁትን በመጥቀስ ሳይሳተፉ ቀርተዋል።

በስብሰባው ላይ የተሳተፉት መሳሪያቸውን እንዲያስመዘግቡ እና ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ሠራዊት ጋር ለመዋጋት እንዲዘጋጁ ታዘዋል። ሆኖም ግን የኦሮሞ ነዋሪዎች ኦነሠ ጉዳት እንዳላደረሰባቸው በመከራከር ጠንከር ያለ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን፣ ይልቁንም በአካባቢው ትክክለኛው ጥቃት ፈፃሚው እራሱን የደራ ፋኖ እያለ የሚጠራው ቡድን መሆኑን ገልፀዋል። ለእነዚህ ተቃውሞዎች መልስ የሰጠው አቶ ተስፋዬ በበኩሉ ነዋሪዎቹን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ትደግፋላችሁ፤ ትሸሽጋላችሁ ብሎ በመወንጀል ውጥረቱን አባብሶታል።

በኦሮሞ ነዋሪዎች ተቃውሞ የተበሳጨው ተስፋዬ ትኩረቱን ወደ አካባቢው የአማራ ነዋሪዎች አዞረ። ስለ ኦነሠ እና የኦሮሞ ማህበረሰብ ጥልቅ እና ሥር የሰደዱ የተዛቡ ጽንሰ-ሀሳቦችን በማቀነባበር፣ በአማራ ነዋሪዎች መካከል ጥላቻን ቀሰቀሰ። ስብሰባው በመንግስት የሚደገፉ ታጣቂዎች እና የአካባቢው የታጠቁ የአማራ ማህበረሰብ መካከል ግንባር የፈጠረና የኦሮሞ ጎረቤቶቻቸውን ለማጥቃት የሚያገለግል የቃል ኪዳን ማሰሪያ እንዲሆን ተደርጎ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ይህ መድረክ የበለጠ ብጥብጥ እና ክፍፍልን ለመፍጠር ሆኔታዎችን  ያመቻቸ ነበር።

  • የችግሩ መባባስ

ሌ/ጄኔራል ተስፋዬ በአጸፋው በስብሰባቸው ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆኑትን እና የጦር መሳሪያ እንዲያስመዘግቡ፣ ብሎም ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን እንዲዋጉ ያቀረቡትን ሃሳብ ውድቅ ያደረጉ የኦሮሞ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር እና የከባድ መሳሪያ ድብደባ ዘመቻ ጀመሩ። ይህ ዘመቻም ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ቤተሰቦች ወደ ምድረ በዳ በማፈናቀል ያለመጠለያና የደህንነት ጥበቃ እንዲቀሩ አድርጓል። ነዋሪዎቹ ከሸሹ በኋላ እንኳ መሸሸጊያ በሚፈልጉበት ቁጥቋጦዎች ውስጥ የከባድ መሳሪያ ድብደባ ተከትሏቸው ቀጥሎ ነበር።

  • የአንገት መቅላት ወንጀሎችን በተመለከተ

በወጣቱ ደረጄ አማረ ላይ ብቻ የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊት የሚያሳየው ቪዲዮ በቅርቡ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ብቅ ብሎ የነበረ ቢሆንም፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ባደረገው ምርመራ የሰረርኩላ መንደር ነዋሪ በሆነው ታደሰ ንጉሴ በተባለ ወጣት ላይም ሌላ ተመሳሳይ የአንገት መቅላት የተፈፀመ መሆኑን ለማወቅ ችሏል። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ሁለቱንም ቪዲዮዎች መዝግቧል።

ምንም እንኳን ትክክለኛው ቀን በእርግጠኝነት ባይታወቅም እነዚህ አሰቃቂ ድርጊቶች የተፈጸሙት የዛሬ ሁለት ወር ገደማ እንደሆነ ይገመታል። ለእነዚህ ዘግናኝ ወንጀሎች የደራ ፋኖ ነን የሚሉ እና እንደ አለማየሁ አያሌው ባሉ የአገዛዙ ተላላኪዎች የሚደገፉ ግለሰቦች ተጠያቂ መሆናቸውን የመጀመሪያ ግኝታችን ያመላክታል።

  • የወንጀሎቹ አፈፃፀም ሁኔታ

የደረጄ አማረን አረመኔያዊ የአንገት መቅላት እና በሰሜን ሸገር ሰላሌ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃት የሚያሳዩ የቆዩ ቪዲዮዎች በቅርቡ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መውጣታቸው ያልታሰበ ይመስላል። እንደ ውስጣዊ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ፣ የአገዛዙ የመጀመሪያ እቅድ “የተለያዩ ቋንቋዎችን ቢናገሩም ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና ፋኖ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለማጥቃት በጋራ ይሰራሉ” የሚል ትርክቱን ለማስተጋባት ሲዘጋጅ በነበረው የፕሮፖጋንዳ ዘጋቢ ፊልም ላይ እነዚህን ቪዲዮዎች ለመጠቀም ነበር። ነገር ግን፣ ቪዲዮዎቹ ሾልከው ከወጡ በኋላ፣ አገዛዙ ስትራቴጂዎቹን ለመቀየር ተገዷል። ቀረጻውን ያዘጋጀው ህዝባዊ ቁጣን ለመቀስቀስ እና በአካባቢው በሚገኙት በሁለቱ ትላልቅ ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ልዩነት እና በአጠቃላይ ሀገሪቱ ያለውን መከፋፈል ይበልጥ ለማባባስ ነበር። ነገር ግን፣ አገዛዙ ከጠበቀው በተቃራኒ፣ አብዛኛው የህዝባዊ ቁጣው በራሱ በአገዛዙ ላይ ያነጣጠረ ነበር። ብዙዎች ከእነዚህ ክስተቶች በስተጀርባ ያለውን ሆን ተብሎ የተቀናጀ እና አገዛዙ አሳዛኝ ክስተቶችን ለፖለቲካዊ ጥቅም ለመጠቀም የሚያደርገውን ሙከራ ተገንዝበዋል።

. ትንተና

  1. ታሪካዊ አውድ፡-

እነዚህ በምርምራ የደረስንባቸው ግኝቶች፣ ከዚህ በፊት የአብይ መንግስት አንድም ተቃዋሚዎችን ለማጉደፍ እና አንድምበፕሮፓጋንዳ የተደገፈ የጎንዮሽ ግጭቶችን ለመቀስቀስ ከሚጠቀምባቸው የተለመዱ ስልቶች ጋር የሚጣጣም መሆኑን ያሳያሉ። ለአብነት ገዥው ቡድን ሀሰተኛ ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተዋናዮችን በማሰማራት አስነዋሪ ድርጊቶች እንዲፈጽም የማድረግ ታሪክ ያለው ሲሆን፣ በመቀጠል ደግሞ እነዚህን አስነዋሪ ወንጀሎች ከኦነሠ ጋር አያይዞ በማቅረብ የተዛቡ የመረጃ ዘመቻዎች ያከናውናል።

በተለይም እንደዚህ አይነት ክስተቶች በቀደመው ዘመን በጉልህ የማይታዩ እና በስፋት የታዩት የአብይ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ መሆኑ ደግሞ የራሱ ትርጉም አለው። ይህ የተቀነባበረ ትርክት እና የተቀነባበረ የኃይል እርምጃ ገዥው አካል የህዝቦችን መተባበር አዳክሞ ለመከፋፈል እና የትኩረት አቅጣጫን ከሥራዓቱ ውድቀቶች እና ከግጭት አፈታት ቀይሮ ለማዘናጋት በተሳሳተ መረጃ ላይ እምነት እንዲኖር ለማድረግ መሆኑን ያሳያል።

  • የሰሞኑ ጥቃት አነሳስ

በመጀመሪያ ለአገዛዙ ፕሮፓጋንዳ ዶክመንተሪ የታሰቡ ቪዲዮዎች ሾልከው መውጣታቸውን ተከትሎ፣ የውስጥ ኢንተለጀንስ ምንጮች እንደሚጠቁሙት፣ የአብይ መንግስት አካሄዱን በፍጥነት አስተካክሎ በኦሮሞ እና በአማራ ማህበረሰቦች መካከል የጎንዮሽ ግጭት ለመፍጠር  ተጠቅሞበታል። ይህ የተሰላ የስትራቴጂ ለውጥ በሁለት ምክንያቶች የተነሳ ይመስላል፡-

  1. አገዛዙ “በኦሮሚያ ውስጥ ያለውን ስራ ለመጨረስ” በሚል እራሱ በራሱ ላይ የጣለው የ2-3 ወራት የጊዜ ገደብ ከወታደራዊ ክንዋኔዎች አንጻር ሲታይ ብዙም ሳይቀናው ገደቡ እየቀረበ በመሆኑ ነው። ገዥው ቡድን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየገጠመው ካለው ሽንፈትና ውድቀት የተነሳ በሚፈጥራቸው የጎንዮሽ ግጭቶች የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር እና ለውድቀቶቹ መውጫ ምክንያት ለመፍጠር በመፈለጉ ነው።
  • ኦሮሚያን ጨምሮ በመላ አገሪቱ ውስጥ በአገዛዙ ላይ እየተስፋፋ የመጣው አመፅ ወደ ዋና ከተማዋ እየተቃረበ ነው። ቅርብ ጊዜ በአገዛዙ በሚደገፍ ከፍተኛ ነጋዴ ላይ የደረሰው የቦምብ ፍንዳታና የመሳሰሉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ክስተቶች በአገዛዙ የመጨረሻ ምሽግ ላይ ያለውን ስጋት አጉልተው ያሳዩ ናችው። ገዥው ቡድን የህብረተሰቡን ትኩረት ወደ እርስ በርስ ግጭት በማዘዋወር፣ እነዚህን ስጋቶች ለማቃለል እና እየባሰበት ያለውን ፍርሃቱን ለመግታት ባለመ ሥራ በመጠመዱ ነው።

ሐ. ምክረሃሳብ

  • ለገለልተኛ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፡-

ስለ መፈናቀሉ፣ የአየር የቦምብ ድብደባ እና አስነዋሪውን ቪዲዮዎች በአፋጣኝ አጠቃላይ ምርመራዎችን ማድረጉ አስፈላጊ ናቸው። የገዥው ቡድን ድርጊቶች ለአለም አቀፍ ተጠያቂነት መመዝገብ እና ይፋ መሆን አለባቸው።

  • ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ፡-

የአብይ መንግስት ግጭት የማምረት እርምጃ ከአገር ውስጥ የስልጣን ማስጠበቅያ እርምጃ ያለፈ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። የአብይ አህመድ ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ጦርነቶችና የማህበረሰቦች የጎንዮሽ ግጭት መቀስቀስ የኢትዮጵያን መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥላል፣ ይህም በሰፊው በቀጠናው ላይ ትልቅ ተጽእኖ አለው። ጠንካራ አለም አቀፍ ውግዘት እና ጫና የግድ የሚሆነው ለዚህ ነው።

  • ለአማራ ጥቅም ለቆማችሁ ቡድኖች፣ አክቲቪስቶች እና ምሁራን፡-

በኦሮሞ እና በአማራ የፖለቲካ ሃይሎች መካከል ያለው መሰረታዊ የፖለቲካ ልዩነት ሊስተናገድ የሚገባው በተደራጁ የፖለቲካ ሃይሎች መካከል እንጂ ለፖለቲካ ግጭቶች ምንም አይነት ሃላፊነት በማይወስዱ ሰላማዊ ዜጎችን በማጥቃት አይደለም። እነዚህን ዕኩይ ክስተቶች በማቀነባበር የአብይ መንግስት ሚና የሚካድ ባይሆንም ኣንድኣንድ የፋኖ ሚሊሻ ቡድኖች ወደ ኦሮሚያ ተሻግረው የታጠቁ የአማራ ተወላጆችን በኦሮሞ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ለጥቃት ሲቀሰቅሱ ነበር። የአማራ ፖለቲካ ማህበረሰብ የህዝብ ግንኙነት ስልቶቹን በጥሞና በመገምገም፣ አገዛዙ ዕድሜውን ለመቀጠል ሲል የሚፈጥረው የህዝቦች የጎንዮሽ ግጭት እንዲጠቀም እድል ከመስጠት መቆጠብ አለበት። በንፁሀን የኦሮሞ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በማያሻማ መልኩ መወገዝ አለበት።

አሁን ያለው የብጥብጥ ሆኔታ ዘላቂነት የሌለው እና አጥፊ ነው። ህዝባችን ላይ ወደር የለሽ የተቀናጁ ጥቃቶችን ተፈጽመው ለከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ይገኛል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም፣ እራሱን ‘የደራ ፋኖ’ ብሎ በሚጠራው የሽፍቶች ቡድን ላይ እርምጃ መውሰድ የጀመረ ሲሆን ወደፊትም የገዢው ቡድን ባዶ ትርክቶችና ተንኮሎችን በማጋለጥ የንጹሃንን ህይወት መታደግ አጠናክሮ ይቀጠላል።

ኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛ ዕዝ

ህዳር 22፣ 2024

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading