• Wed. Apr 22nd, 2026

ሞያሌ እና ሌሎች የድንበር ጉዳዮችን በተመለከተ (የኦነግ-ኦነሠ መግለጫ)

Jul 31, 2025

አብይ አህመድ፣ የኦሮሞ ተራማጅ ሀይሎች መሰባሰብ የህልውና ስጋት እንደሚፈጥርበት ስለሚገነዘብ፣ እርስ በርስ የሚያጋጩ ተከታታይ ቀውሶችን በመፍብረክ የኦሮሞን ፖለትካዊ የሃይል አንድነት ለመበጣጠስ የተለያዩ ዘመቻዎችን ሲያካናውን ቆይቷል።

ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ)፣ እ.ኤ.አ. ከ 2019/20 ጀምሮ ሁነኛ ሃይል ለመገንባት፣ ፈጣን የመልሶ ማዋቀር እና የማደራጀት ሂደት እያካሄደ በነበረበት ወቅት፣ አብይ በመንግስት የተደገፈ “ሸኔ” ፈጥሮ በማሰማራት በአማራ ንፁሀን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ የተቀነባበረ ጥቃት እንዲፈፅም በማድረግና ጉዳት በማድረስ ነበር ምላሽ የሰጠው። እንደዚህ አይነቱ የተቀነባበረ ጥቃት በኋላ ላይ የትግራይን ጦርነት ለማስጀመር ውሎ ነበር።

ሰፋ ያለ የተጋዮችና ተቃዋሚዎች የፖለቲካ አጋርነትን ለማደናቀፍ ከተደርጉ የቅርብ ጊዜ የአገዛዙ ጥረቶች መካከል በመሳሪያ የተደገፈ የሃይማኖት ግጭት መልክ የያዙ፤ ለምሳሌ የዝቋላው መነኮሳት ግድያ እና በአርሲ እና በጅማ የሃይማኖት ግጭቶችን ለመቀስቀስ የተደረጉ ሙከራዎች እናስታውሳለን። በጎሳ እና በሃይማኖት ልዩነት የማይገደብ ሰፋ ያለ የተቃውሞ ጎራ የተቀናጀ እንቅስቃሴና ትብብር እንዳይፈጠር ለማደናቀፍ ይረዳው ዘንድ በህብረተሰብ ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን ለግጭት ቀስቃሽነት እንዲውሉ አድርጎ በግልፅ ይጠቀማቸዋል።

የሰሞኑ የሞያሌው ገዳይ በኦሮሞ-ሶማሌ ህዝቦች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረው የአገዛዙ ቀጣይ የእርስ በርስ የማጋጨት ሴራ ነው። ለሶማሌ ወንድሞቻችን፡ በስማችሁ የሚጠቀመውን የግጭት ተንኮል ሁሉ አትቀበሉ። አቢይ የሚጠቀመው ከሁሉቱ ህዝቦች የእርስ በርስ ግጭት ሲሆን እሱ የየትኛውንም ህዝብ ጥቅም አይውክልም።

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከአገዛዙ የጥፋት አጀንዳ ጋር ለሚሰለፉ ጥቂት የኦሮሞ ተዋናዮች፡ ቆም ብላችሁ አስቡ። በድንበራችን ላይ ምንም አይነት ነፃ የሆነ በራሱ ተነሳሽነት ችግር የፈጠረ የሶማሊ ኃይል የለም። የሁሉም ግጭትና ችግር ጥንስስ ምንጩ አራት ኪሎ ያለው አገዛዝ ሲሆን፣ ለህዝብ እየደረሰ ያለውም በመንግስት ብሮድካስት በኩል ነው። ዓይንህን ክፈት። አብይ በስልጣን ላይ እስከቀጠለ ድርስ የትኛውም የኦሮሞ ጥያቄ አይመለስም።

የኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛ ዕዝ

ሐምሌ 27፣ 2025

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading