• Sun. Jun 7th, 2026

በአርሲ የቀጠለው እልቂት (የኦነግ-ኦነሰ መግለጫ)

Jun 5, 2026

ባለፉት በርካታ ዓመታት በአርሲ–አሳኩ አካባቢን ጨምሮ በመላው ኦሮሚያ ውስጥ –የአብይ አህመድ የካድሬ ኔትወርክ በማህበረሰቡ መካከል ክፍፍልን ለመፍጠር በጀትም መድበው ሲሰራ ቆይተዋል። ኦሮሞዎችን በአማራዎች ላይ፣ ሙስሊሞችን ደግሞ በክርስቲያኖች ላይ ለማነሳሳት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። በኦሮሞ ህዝብ ውስጥም እንኯን ክርስቲያን ቱላማ ኦሮሞን በሙስሊም ኦሮሞ ወንድሞቻቸው ላይ ለማነሳሳት ሞክረዋል። ይህንኑ ለመተግበር ሌላውን በማግለል ጠመንጃ በተወሰነ ቡድን እጅ እንዲገባ ኣድርገዋል። የብልጽግና ፓርቲ በግልጽ የአንድ ማህበረሰብ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ትርክት ለመስራትም ጥረዋል። ይህ ማህበረሰቡን የመሸርሽር ሴራ ለዓመታት የደከሙበት ጉዳይ ነው።

ባሳለፍነው ሰኞ (May 31, 2026) የOLA ኃይሎች በመላው ኦሮሚያ የተጣለውን እገዳ ለማስፈጸም ሲንቀሳቀሱ፣ የአብይ አህመድ ካድሬዎች እድሉን ተጠቀሙበት። ለዓመታት የነዙትን የጎሳ እና የሃይማኖት ቅስቀሳ በመጠቀም፣ በኣከባቢው ያሉ የአገዛዝ ባለስልጣናት የማህበረሰብ ግጭትን በንቃት አቀጣጠሉ። ከዚያ የተነሳ የንጹሃን ህይወት በከንቱ እንዲጠፋ አድርገዋል። የተለመደው የዐቢይ አህመድ የድንቁርና ተግባር ነው።

ዛሬ፣ በመላ አገሪቱ ያሉ ተቃዋሚ ኃይሎች የጎንዮሽ ግጭቶችን ውድቅ ማድረጋቸው ብቻ፣ በአብይ አህመድ የሽብር አገዛዝ ላይ ምንም አይነት የተቀናጀ እርምጃ ሳይወሰድም፣ ዐቢይ አህመድ ህዝቦችን የሚከፋፍልበት ምክንያት እያጣ መሆኑን እያወቀ ነው። የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ተብዬ ፡ የኦሮሞ ኣባጋዳዎችን በቀጥታ ኣስገድሎ በOLA ላይ ስያላክክ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጭምር ተይዞም የማይማረው የድንኮች ስብስብ፣ አሁን ደግሞ “ምርጫችንን ለማደናቀፍ የተሰማሩት ኃይሎች ቤተክርስቲያንን ኢላማ አደረጉ” በማለት ልክ አብያተ ክርስቲያናት የምርጫ ማጭበርበር ቦታዎች የሆኑ አስመስሎ ተሳልቀዋል።

ከጅምሩ፣ አቢይ አህመድ በ2018 ከኦነግ-ኦነሰ ጋር የተጀመረውን የሰላም ሂደቱን ሲያዛባ ሁለት ግቦች ነበሩት። አንደኛ፣ በኦሮሚያ ውስጥ ማንኛውንም የፖለቲካ ተቃዋሚ ለመጨፍለቅ OLA በጫካ መቀጠል እንደ ምክንያት ለመጠቀም ነበር። በግዜው በግልጽ “ህወሃት በትግራይ ውስጥ የፖለቲካ ህይወትን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ለ27 ዓመታት ገዝቷል። በኦሮሚያም እንዲሁ እናደርጋለን” ሲል ነበር። ሁለተኛው ዓላማ OLAን በአማራ ላይ እንደ ምናባዊ ጠላት አድርጎ መጠቀም ነበር። የሄንንም ዐቢይ አህመድ በዝግ ሲለው ነበር ፣ “አማራው ካልተንበረከከ፣ ይቃጠላታል፤ እና OLAን እንደ አማራጭ እንደሚመርጡ እናሳያቸዋለን።”

ከአማራ እና ከሌሎች ኃይሎች ጋር የፖለቲካ ልዩነቶች አሉን። ይህ ጤናማ እና ተፈጥሯዊ ነው። ይቀጥላሉም። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ፣ አንድ ቦዘኔ አማሮችን እንዲገድል እና ኦሮሞዎችን እንዲወቅስ፣ ኦሮሞዎችን እንዲገድል እና አማሮችን እንዲወቅስ፣ የመከፋፈል ትርክቶቹን ተራ በተራ እየገዛንለት፣ በመሃከል የኣያሌ ንጹሃንን መቀጠፍ ስንፈቅ፣ ስናስችል ኖረናል። ያ ዘመን አልፏል። ለወደፊቱም እንዳይሳካ በትጋት መሰራት ኣለበት። የፖለቲካ ልዩነቶች ምንም ይሁኑ ምን፣ ሁላችንም በሰው ልጅ ሕይወት ክቡርነት እና ልዕልና ላይ የጋራ ስምምነት አለን።

የኦነግ፡ኦነሳ ከፍተኛ ዕዝ
ሰኔ 4 2026

Oromia #Ethiopia

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading