አብይ አህመድ ይህንን ምርጫ ተብዬ እስከመጨረሻው በመግፋት ቀጥሏል። ይህ ተውኔት የሚከየነው፣ አገሪቱ በእርስ በርስ ጦርነት የመበታተን ጫፍ ላይ ባለችበት፣ ወሳኝ ሚና ያላቸው ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመሳተፍ ፈቃደኛ ባልሆኑበት፣ በእጅ የተሰየሙትን የምርጫ ቦርድ አመራር ጨምሮ የተቋማዊ ማዕቀፍ በስብሶ በቀጠለበት፣ የፓርላማ መቀመጫዎች አንድ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት አስቀድመው በተከፋፈሉበት፣ እና ህዝቡ በግዳጅ ምርጫ መንገላታትን እንደማይታገስ በማያሻማ ሁኔታ ግልጽ ባደረገበት አውድ ውስጥ ነው። በተጨማሪ፣ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታመን ታዛቢ የማይታደመው “እከሌ አየልኝ” ለማለት እንኯን ያልበቃ መካን ተውኔት ነው።
በዚህ አውድ ዉስጥ ወደፊት የሚገፋው ምርጫ ተብየ፤ ተራ ተውኔት ብቻ ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን የፖለቲካ ወንጀል ነው። በራሱ በህዝቡ ጥሪት የተከፈለ እና ህዝቡ ላይ የሚፈጸም ከፍተኛ የፖለትካ ወንጀል ነው።
በዚህ መንገድ አብይ አህመድ በሕዝባችን ሲያፌዝ፣ የጋራ ሀብታችንን ሲያባክን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል። በዚህ መሰረት፣ ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ተግባራዊ የሚሆን የትራንስፖርት እና የእንቅስቃሴ እግድ በመላው ኦሮሚያ ታውጇል። ማንኛውም ተሽከርካሪ፣ እና የንግድ ትራፊክ የታገደ ይሆናል። በሰብአዊ ፕሮቶኮሎች ስር የሚሰሩና ጽኑ ታማሚ የያዙ አምቡላንሶች በብቸኛ ልዩነት ይታያሉ። ከዚው ውጪ የትኛውንም እገዳ መጣስ ፈጣን እና ወሳኝ እርምጃን ያስከትላል።
በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ በዋና ከተማው ውስጥ ያሉ ሁሉም የዲፕሎማቲክ ኮር አባላት በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ ኦሮሚያ ወይም በኦሮሚያ ውስጥ የሚደረገውን ማንኛውንም ጉዞ ያለምንም ልዩነት እንዲያግዱ እንመክራለን።
የኦነግ-ኦነሳ ከፍተኛ ኮማንድ
ግንቦት 29፣ 2026
Oromia #Ethiopia

