• Fri. Sep 18th, 2026

ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የተሰጠ መግለጫ (የኦነግ-ኦነሰ መግለጫ)

Sep 17, 2026

ወለጋ፡ በሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል ከተሰማራባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው ወለጋ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በአገዛዙ የሚደገፉ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ ኃይሎች በተለያዩ አደረጃጀቶች ሲንቀሳቀሱበት ቆይቷል። ከእነዚህም መካከል በአማራ ስም እንደሚንቀሳቀስ እና በኦሮሞ ሲቪሎች ላይ በሚፈጽመው ጥቃት የሚታወቅ አንድ አነስተኛ የታጠቀ ቡድን ይገኝበታል። ይህ ቡድን በመጀመሪያ የተቋቋመው፣ የሰለጠነው፣ የታጠቀው እና የተሰማራው በአገዛዙ ሲሆን፣ ዓላማውም ከህወሓት ኃይል (TDF) እና ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (OLA) ጋር በሚደረገው ጦርነት ወቅት የOLA እንቅስቃሴ ለመግታት እንዲያግዝ ነበር። በአማራ ክልል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው የቡድኑ አባላት ከአገዛዙ የሚሊሻ መዋቅር በይፋ የተለዩት።

ከይፋ መዋቅሩ ሲለዩ አገዛዙ አካሄዱን ቀየረ። ቡድኑን በቀጥታ የሚሊሻው አካል አድርጎ ከማሰማራት፣ በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ የኦሮሞን ህዝብ ለማነሳሳት እንደ መሳሪያ መጠቀም ጀመረ። ትክክለኛው አድራጊ አካል ማንነት ሳይረጋገጥ ጭምር፣ በኦሮሞ ሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችን በሙሉ በዚህ ቡድን ስም አጠናክሮ ገፋበት። እንዲህ ባሉ ጭካኔ የተሞላባቸው ድርጊቶች የሚፈጠረውን የህዝብ ቁጣ የፖለቲካ ጥቅም የተረዳው አገዛዙ፣ ይህንን ኃይል በህይወት የማቆየት ስልታዊ ፍላጎቱ እየጠነከረ መጣ። ይህንንም ለማስቻል፣ መከላከያ ሠራዊት ወይም የኦሮሚያ ኃይሎች ቡድኑን “ለመዋጋት” እንዲንቀሳቀሱ ከታዘዙ በኃላ፣ መሳሪያዎችን እና ሌሎች ሀብቶችን ትተው እንዲወጡ ይታዘዙ ነበር። እንዲሁም፣ ቡድኑ ገንዘብ እና መሳሪያ እንዲዘርፍ የሚያስችሉ መረጃ የማሾለክ ስራ ሲሰራቆይቷል። ቡድኑ በድርጊቱ እና በሚጠቀምበት ስም ጭምር በግልጽ በያዘው የፀረ-ኦሮሞ አቋም፣ ከአገዛዙ ቀጣይነት ያለው ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ድጋፍ ሳይኖር በኦሮሞ ህዝብ መካከል መቆየቱ ፈጽሞ የማይቻለው ነው።

በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የትብብር ውይይቶች መነሳት ሲጀምሩም፣ አገዛዙ ተመሳሳይ ስልቱን አጠናክሮ ቀጠለ። አለመተማመንን ለማስፋት፣ በማህበረሰቦች መካከል ውጥረትን ለማባባስ እና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል ሊኖር የሚችልን ትብብርን አስቸጋሪ ለማድረግ ተደጋጋሚ የጭካኔ ድርጊቶች ተፈጸሙ።

ከኣባይ ማዶ ያሉ የአማራ ኃይሎች፣ የራሳቸውን ቋንቋ የሚናገር፣ የታጠቀ ቡድን ተመልክተው፣ ተጽዕኖአቸውን ከአማራ ክልል ውጭ አሰፋን ለማለት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቀሙበት እንጂ እርምጃው የሚያስከትለውን የረጅም ጊዜ የፖለቲካ ውጤት ከግምት ውስጥ አላስገቡም። ከእንደዚህ ዓይነት ቡድን ጋር በመተባበር፣ ሊገኝ ከሚችለው የአጭር ጊዜ ወታደራዊ ጥቅም እጅግ የላቀ የፖለቲካ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል አደጋ ያለው በመሆኑ የአማራ ሃይሎች ይህን ቡድን በተመለከተ የሚያደርጉትን ኃላፊነት ከጎደለው የሚዲያ ንግግሮች እንዲታቀቡ እና ከዚህ ቡድን ጋር ያላቸውን ግንኙንት በግልጽ እንድያቋርጡ ጥሪ እናቀርባለን።

ጽምዶ ፦ OLA በጽምዶ ውስጥ ምንም ዓይነት ተሳትፎ የለውም፤ የዚህ አካልም አይደለም። ነገር ግን OLAን ያካተተው ከምዕራብ እስከ ምስራቅ እና ከደቡብ እስከ ሰሜን የሚዘልቁ የተቃዋሚ ኃይሎች ትብብር ለህልውና ምስረታ በመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

እየተፈጠረ ያለው ትብብር በሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። አንደኛ፣ የተቃዋሚ ህዝባዊ ኃይሎች እርስ በርስ የሚያደርጉትን ሽኩቻ አቁመው፣ ጥረታቸውን የሁሉም ህዝቦች የጥፋት ምንጭ ወደሆነው አገዛዝ አቅጣጫ እንዲያተኩሩ ነው። ሁለተኛ፣ የአገሪቱ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄዎቹን በቀጥታ በመሳተፍ የሚፈታበትን ሰፊ መሰረት ያለው የሽግግር መድረክ መፍጠር ነው። የህዝባዊ ሃይላት አፋጣኝ ኃላፊነት ከሰማይ በታች ያሉ ሁሉም የህዝቦች ጥያቄዎች በእነርሱ ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚፈቱበትን የፖለቲካ እና የደህንነት ዐውድ መፍጠር ነው።

በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው የሲቪል ህዝብ የማስታጠቅ ዘመቻ: OLA በሚንቀሳቀስባቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች ሁሉ፣ አብይ አህመድ ሲቪሎችን የማስታጠቅ እና የማሰባሰብ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዙ አሁን በስፋት የታወቀ ጉዳይ ሆኗል። ግን አዲስ ፖሊሲ አይደለም። ይህ አሰራር ቢያንስ ከ2021  ጀምሮ የነበረ ሲሆን፣ አገዛዙ “የአማራ ሲቪሎችን ለመጠበቅ” በሚል ሰበብ ተመሳሳይ ዲርጊቶችን ሲፈጽም ቆይቷል።

ዋናው ጉዳይ አብይ አህመድ በመደበኛ የጸጥታ ኃይሎች ላይ ብቻ መተማመን እንደማይችል አምኖ መቀበሉ አይደለም። ያ እውነታ ለዓመታት ግልጽ ነበር። ከአምስት ዓመታት በፊት ጀምሮ፣ በአገዛዙ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ መደበኛ ያልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች በኦሮሚያ ማፍላቱ ይህንን አምኖ የመቀበሉን በተግባር መስክረው አልፏል። አሁን ያለው አጣዳፊ ተግባር፣ አገዛዙ በከፍተኛ ስጋት ለመደበቂያነት እየፈለገ ካለው የኦሮሞ ህዝብ በማያሻማ መልኩ የመነጠል ነው። አብይ አህመድ ከኦሮሞ ህዝብ ጀርባ እንዲደበቅ መፈቀድ የለበትም። ስለዚህ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የልዩነቶች መነሻ የሆኑ የመከፋፈያ አጀንዳዎችን ለይቶ ወደ ጎን መተው እና በሁሉም ንግግሮቻቸው እና ተግባሮቻቸው አገዛዙን ከህዝቡ በጥንቃቄ የመለየት ሃላፊነት ይኖርባቸዋል።

የኦነግ፡ኦነሳ ከፍተኛ ዕዝ
ሴፕቴምበር 17, 2026
#Oromia #Ethiopia

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading