በኦሮሚያ፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን ራሱን “የወለጋ ፋኖ” ብሎ የሚጠራው በመንግስት የሚደገፈው ታጣቂቡድን በሰላማዊ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው የሃይል እርምጃ መቀጠሉን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ይገነዘባል።ይህ የጥፋት ቡድን በመጀመሪያ የተደራጀና፣ የታጠቀው በአገዛዙ ሲሆን ከአብይ መንግስት የሚያገኘውየሎጂስቲክስ ድጋፍም ቀጥሎ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም በአገዛዙ የሚሊሺያ ኃይል ውስጥ መደበኛቦታዎችን ይዞ የነበረና በአካባቢው ላለው አለመረጋጋት አንዱ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
የዚህ ሚሊሻ ህልውና ያስፈለገበት የገዥው ቡድን ስልታዊ አላማዎች በዋናነት ሁለት ናቸው። እነሱም፦
1. በአከባቢው ባለው የኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ የፍርሀት ድባብ እንዲሰፍን በማድረግ በኦሮሞ ነጻነትሠራዊት (OLA) በሚመራው ቅቡልነት ባለው የነጻነት እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ እናተሳትፎን ለማፈን እና፣
2. በህዝቦች መካከል በተለይም በሁለቱ የአገሪቱ ትላልቅ ማህበረሰቦች መካከል ያለውን አብሮነትለመሸርሸር እና የጎንዮሽ አለመግባባት/ ግጭትን ለመፍጠር የተነደፈ የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር እናእንዲቀጥል ማድረግ ነው።
በመሆኑም የዚህ ሚሊሻ ተግባር በህዝባችን ላይ መሰረታዊ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል። ይህንን ወንጀለኛ ቡድን የፈጠረው እና በቀጣይነት ህልውና እንዲኖረው የሚያስችለው ቀዳሚ አካል አገዛዙበመሆኑ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ለእነዚህ እኩይ ተግባራት በቀጥታ አገዛዙን ተጠያቂ ያደርጋል።
ስለዚህ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA)፤ ሰለማዊ ህዝብን ከነዚህ በመንግስት የሚዘወሩ/የሚደገፉ የጥፋትሃይሎች ጥቃቶች ለመጠበቅ ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎች ለመውሰድ አሻሚ ያልሆነ መብትና ሀላፊነትያለው መሆኑን ያሳውቃል። በመሆኑም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የአገዛዙን አጥፊና ከፋፋይ ጥቅምበሚያስጠብቅ ማንኛውንም ቡድን ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን። ይህ ታጣቂ ሚሊሻ በመንግስትየሚደገፍ የሽብር መሳሪያ መሆኑን ሁሉም ኃላፊነት የሚሰማቸው የፖለቲካ ተዋናዮች እና የሲቪክድርጅቶችም፣ በዚሁ ልክ እንዲያውቁት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የኦነግ-ኦነሠ ከፍተኛ ዕዝ
ኦገስት 28 ቀን 2025
