• Sat. Jun 6th, 2026

የአብይ አህመድ የወለጋ ጉብኝት (የኦነግ-ኦነሠ መግለጫ)

Feb 20, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና የተላላኪነት በጥባጭነቱን እንዲያቆም፣ በቱርክ ፕሬዝዳንት ማስጠንቀቂያ በተሰጠው ማግስት፣ አብይ አህመድ በምዕራብ ወለጋ የሚገኙ ጥቂት ቦታዎችን መጎብኘቱን ተናግሯል። ይህንን ያደረገው ለሦስት ምክንያቶች ነው፡፡

1) ሾልኮ ወለጋ ገብቶ በመውጣት በምዕራብ ኦሮሚያ ላይ ቁጥጥር እንዳለው በሚዲያዎቹ ማራገብ። ሙከራው የተለመደ ማጭበርበር ነው። ሆኖም በሄሊኮፕተር መጥቶ በድብቅ በካድሬ እና ወታደር በታጠሩ ውስን ቦታዎች ላይ በመታየት ሊረጋገጥ የሚችል ምንም ቁጥጥር የለም። የሰፈር ሽፍታም ለተወሰኑ ሰዓታት የተወሰኑ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ ማዘፈን ይችላል። እንዲያውም ከዚህ ጉብኝት የምንረዳው፣ አብይ አህመድ በኦሮሚያ ትርጉም ያለው አስተዳደር መዘርጋቱን የሚያሳዩ ማጭበርበሪያዎች እያለቁበት መምጣታቸውን ነው።

2) “የኦሮሚያውን ጦርነት ያስከተሉት ችግሮችን በመነጋገር መፍታት እንችላለን” የሚለው ለረጅም ጊዜ የተለመደውን አሰልቺ ቅጥፈቱን ለማስተጋበት ነው። ይህ ነጭ ውሸት መሆኑ በተጨባጭ በተደጋጋሚ ተጋልጧል። አብይ አህመድ የኦሮሚያን ችግር በሰላም እንፍታ ብሎ ሲል፣ የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጥያቄዎቹን ትቶ ለድንቁርና አጀንዳው ይስገድ ማለቱ እንደሆነ፣ አይነ፡ልቦና ያለው ሁሉ አይቷል። ዛሬም እንደገና መዋሸት ያስፈለገው በኦሮሞ ካምፕ ውስጥ አሁንም ዋሽቶ ለማታለል የሚፈልጋቸው በድኖች አሉ የሚል ድንቁርና ብቻ ነው።

3) ሁልግዜ እንደሚያደርገው፣ በዛሬው ንግግሩም የኦሮሞን ጥቅም ለማስጠበቅ የቆመ መስሎ በመቅረብ፣ ሕዝባችንን ከሌሎች ብሄሮችና ህዝቦች ጋር ለማጋጭት ነው። በዛሬው መልዕክቱ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለውን ውጥረት ኣስታኮ “የኦሮሞ ጠላቶች ያገኘውን ዕድል ሊነጥቁት አሰፍስፈዋል” ሲል ተናግሯል። ከዚህ በፊትም ብልፅግና ፓርቲ በብቸኝነት የኦሮሞ ለማስመሰል ያደረጋቸው ተደጋጋሚ ጥረቶች ሳይሳኩ ቀርተዋል። የኦሮሞ ህዝብ መብት እና ጥቅም ዋነኛ ጠላት እራሱ አብይ አህመድ ነውና።


የኦነግ ኦነሠ ከፍተኛ ዕዝ
የካቲት 18, 2026

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading